የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች ለተጠቀሱት እቃዎች የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Purchases
- Posted Date : 02/06/2023
- Closing Date : 02/23/2023
- Phone Number : 0114167345
- Source : Reporter
Description
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
በድጋሜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር:- ኢንሥኮ- ማእከል ግዥ ብ/ግ/ጨ/15/2015
ኮርፖሬሽናችን ከዚህ በታች ለተጠቀሱት እቃዎች የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን ፣ ዪፒ ኤስ፣ ኔትዎር ኬብል፣ ፕሮጀክተር ፣ ፋክስ ማሽን እና ተያያዥ እቃዎችን /Disc top Computer, Laptop Computer, Printer፣ Photo Copy Machine፣ UPS, Network Cable , Projector with display፣ Fax Machine and related goods.
በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፋ ለ2015 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ጨረታዉ እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ስራ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ስርተፍኬት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ የሚጠበቅባቸዉ ሲሆን እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የፋይናንሻል ሰነዳቸዉን ለብቻ በፖስታ በማሸግና የፋይናንሻል ሰነድ መሆኑን በመግለጽ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሚወዳደሩበት ኮምፒውተርና ተያያዝ እቃዎች የማይመለስ ብር 400.00(አራት መቶ ብር) በመክፈል ከጥር 29/2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት ከ7፡00-10፡30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ ብሎክ 1 ቢሮ ቁጥር 206 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ (አድራሻው ከስር ተገልጿል፡፡)
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ የካቲት 15 ቀን 2015 ከጧቱ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ለተጠቀሰው፡- ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር, ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን ፣ ኔትወርክ ኬብል፣ ፕሮጀክተር ፣ ፋክስ ማሽን እና ተያያዥ እቃዎችን ግዥ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሽህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ዋጋ ፋይናንሻል፤ ቴክኒካል ፤ኦርጅናል እና ኮፒ ሠነዶችን በተለያየ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከጧቱ 4፡30 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጧቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናዉ መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ከዋና የመወዳደሪያ ሀሳብ (ኦሪጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች ብዛት 1(አንድ)
- አሸናፊዉ ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን 10 ፐርሰንት /አስር ፐርሰንት በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ዉሉን የሚፈጽሙ ይሆናል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብረቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የግዥና ንብረት አስተዳደር ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ቡድን አስተባባሪ
ደብረዘይት መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 011 416 73 45/011 466 9336
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ