የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከ5000 በላይ የሆኑ የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን (የፊያት፣ የAutomotive and Refrigerators/ እና የሌሎችም ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች) በጨረታ በማወዳደር ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-trading-Business-corporation-logo-1

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 11/16/2022
 • Phone Number : 0114167347
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/25/2022

Description

የ ጨ ረ ታ   ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከ5000 በላይ የሆኑ የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን (የፊያት፣ የAutomotive and Refrigerators/ እና የሌሎችም ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች) በጨረታ በማወዳደር ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡

 1. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል ከኀዳር 8 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ ኀዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ዘወትር ከዋናው መ/ቤት /አዲስ አበባ/ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሠዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ኀዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡30 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለተጠቀሱት ዕቃዎች ብር 50,000.00 /ሃምሣ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Security/ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ማሳየት አለባቸው፡፡
 5. ጨረታው ኀዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጧቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች በጨረታው ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያ በ 10 /አሥር/ የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ከ15ኛው ቀን በኋላ ላላነሱበት ቀን በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ቅጣት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
 7. የመጫኛ እና ተያያዥ ክፍያዎች በአሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
 8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-4-16-73-47/ 011-4-66-93-36 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የግዥ፣ ንብረትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ቡድን አስተባባሪ

አድራሻ፡- በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት-አዲስአበባ