የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን አገልግሎት የማይሰጡ ጎተራ-አዲስ አበባ በሚገኘው ግቢ ውስጥ በሚገኙ 10 ኮንቴይነሮች ውስጥ ያሉ ሰነዶች/ወረቀቶች እና ቦክስ ፋይሎች ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-trading-Business-corporation-logo

Overview

 • Category : Disposal Sale
 • Posted Date : 11/16/2022
 • Phone Number : 0114167347
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/28/2022

Description

የ ጨ ረ ታ   ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን አገልግሎት የማይሰጡ ጎተራ-አዲስ አበባ በሚገኘው ግቢ ውስጥ በሚገኙ 10 ኮንቴይነሮች ውስጥ ያሉ ሰነዶች/ወረቀቶች እና ቦክስ ፋይሎች ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልግ ህጋዊ ድርጅት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለበት፡፡

 1. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት ብር/ በመክፈል ከኀዳር 9 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ ኀዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ዘወትር ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ከዋናው መ/ቤት /አዲስ አበባ/ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሠዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ኀዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡30 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 4. ተጫራቾች ንብረቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ባለበት ሁኔታ ወይም ቦክስ ፋይሉንና ወረቀቱን በመለየት ለመግዛት በአካል ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ንብረት 20,000.00 /ሃያ ሽህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
 6. ጨረታው ኀዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጧቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 7. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች በጨረታው ያሸነፉበትን ሙሉ ክፍያ በ 10 /አሥር/ የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ከ15ኛው ቀን በኋላ ላላነሱበት ቀን በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ቅጣት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
 8. አስፈላጊ የሆኑ ማንኛውም ወጪዎች እንዲሁም ቦክስ ፋይሉንና ወረቀቱን በተናጠል መግዛት የሚፈልግ ድርጅት የመለያ የሠራተኛ ዋጋ፣ የማስመዘኛና የትራንስፖርት ዋጋ በአሸናፊው ተጫራች የሚከፈል ይሆናል፡፡
 9. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-4-16-73-47/ 011-4-66-93-36 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

የግዥ፣ ንብረትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ቡድን አስተባባሪ

አድራሻ፡- በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት

ስልክቁጥር 0114 -16-73-47/011 466-93-36 አዲስአበባ-ኢትዮጵያ