የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሃያ ስድስት (26) የተለያዩ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Commercial-Bank-of-Ethiopia-Logo-9

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 08/26/2021
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 09/22/2021

Description

 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2021/22

የተለያዩ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሃያ ስድስት (26) የተለያዩ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1) ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ነሐሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አለፍ ብሎ በሚገኘው በባንኩ ገራዥ /የቀድሞ አማልጋ ሜትድ/ ግቢ ውስጥ በሥራ ሰዓት ብቻ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡

2) ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሠነድ ቄራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ሠፈር ቅርንጫፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ነሐሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም.ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ተኩል (3፡30) ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡

3) ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የተሸከርካሪ ዓይነት የጨረታ የመነሻ ዋጋቸውን 25% (ሃያ አምስት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (Commercial Bank of Ethiopia) በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4) ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ አሸናፊ ለሆኑት ለሚገዙት ዕቃ ክፍያ የሚታሰብ ሲሆን ተሸናፊ ለሆኑት ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

5) የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥኖች ማክሰኞ መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሁሉም በአንድ ላይ ይዘጋሉ፡፡

6)ተጫራቾች ያስገቡት የጨረታ ሰነድ ማክሰኞ መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ በሚገኘው የጎፋ ሰፈር ቅርንጫፍ የሠራተኞች የመዝናኛ ክበብ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Send me an email when this category has been updated