የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር ከዚህ በታች የተጠቀሱትን፣ የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Commercial-Bank-Of-Ethiopia-Sport-Association-logo

Overview

  • Category : Sports Material & Equip.
  • Posted Date : 10/15/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/25/2022

Description

 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር ከዚህ በታች የተጠቀሱትን፣ የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ግልፅ ጨረታ ቁጥር ቢድ 05/2015

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት የተፈለገው ብዛት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ወይንም ቅድመ ሁኔታ ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና (ብር)
1. የስፖርት ትጥቆች እና ቁሳቁስ 40 ዓይነት 40,000.00

በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ሁሉ

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃዳቸውን፣ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ውስጥ የተመዘገቡበትን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ የማይመለስ ብር 50/ሀምሳ/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር አካውንት ቁጥር 1000010984789 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን  ከሰኞ ጥቅምት 07 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋት 2፡00-6፡00 እና ከሰዓት ከ7፡00-10፡00 ስታድየም ናሽናል ታወር ህንፃ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 223 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ስለጨረታዎቹ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5-58 06 80/ 03 49 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ/ በሲፒኦ ሰነዱ ውስጥ በተጠየቀው መልኩ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታ ቁጥር ቢድ 05/2015 (የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ) ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ከዚህ እንደሚከተለው ተዘግቶ ይከፈታል፡፡ በዚህም መሠረት የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ ሰነዳቸውን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው የፍላጎት መግለጫ ዝርዝር መሰረት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግ ባንክ ስፖርት ማህበር