የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለፁትን እና በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው የተለያዩ ንብረቶችን በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 09/17/2021
- Phone Number : 0113852139
- Source : Reporter
- Closing Date : 09/29/2021
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለፁትን እና በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው የተለያዩ ንብረቶችን በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | ለጨረታ የቀረበው ሕንፃ/ንብረት አገልግሎት | ቤቱ/ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የቦታው ስፋት ሜ2 | የካርታ/የባለቤትነት
ማረጋገጫ ሠነድ ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ | |||
ከተማ | ወረዳ | ቀበሌ | የቤት ቁጥር | |||||
1 | የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ህንፃ | ድሬዳዋ | 02 | – | – | 180,000 ካሬ ሜትር /18 ሄክታር/ | መል/ሊ/2618 | 388,786,577.01 |
2 | የተለያዩ የጨርቃ ጨርቅ ማሽነሪዎች | ድሬዳዋ | 02 | – | – | – | – | 161,407,413.16 |
ጠቅላላ ድምር | 550,193,990.17 | |||||||
3 |
የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ህንፃ | ሰበታ | ዲማ | 1 | – | 17 ሄክታር | L/2413/2001 | 657,727,708.05 |
4 | የተለያዩ የጨርቃ ጨርቅ ማሽነሪዎች | ሰበታ | ዲማ | 1 | – | – | – | 129‚856‚283.40 |
ጠቅላላ ድምር | 787,583,991.45 | |||||||
5 |
ለፋብሪካ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል በግንባታ ላይ ያለ ህንፃ |
ሰበታ |
ሃዋስ |
ሃሮ ጂላ ፋልሶ |
33‚430 ሜ.ካ |
WLBEN/6844/BL9 |
68,949,972.92 |
|
6 | መኖሪያ ቤት | ዋጩ /ም.ሐረርጌ/ | ሀብሮ | 85.5 ካ.ሜ | 140‚356.96 | |||
7 | ንግድ ቤት | ገዋኔ | አፋር | 56.82 ካ.ሜ | 304‚358.66 | |||
8 | መኖሪ ቤት | በዴሣ | 60 | 152‚750.53 | ||||
9 | ንግድ ቤት | ድሬዳዋ | መልካ ጀብዱ | 4‚800.00 | ||||
10 | መኖሪያ ቤት | መተሀራ | ፈንታሌ | 01 | 0186 | 440 | 3873/31/1794 | 441‚640.09 |
11 | መኖሪያ ቤት | መተሀራ | ፈንታሌ | 02 | 250ካ.ሜ | 00/1825/42/1/88 | 119‚887.69 | |
12 | መኖሪያ ቤት | በቆጂ | 560m2 | 965/2011 | 93,473.96 | |||
13 | መኖሪያ ቤት | ከምባታ ጣምባሮ ዞን | ሀይሮ | – | 10/1/3/89 | 189,990,82 |
ማሳሰቢያ
- የንብረቶቹን አጠቃላይ ሁኔታ በግንባር ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ባንኩ የጉብኝት ፕሮግራም እንደ አስፈላጊነቱ ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡
- በተራ ቁጥር አንድ ላይ የተገለፀው ፋብሪካ ከድሬደዋ አስተዳደር ጋር የገባው እና ለስልሣ ዘጠኝ ዓመት /ከ2004 እስከ 2073 ዓ.ም/ የሚቆይ የሊዝ ውል አለው፡፡
- በተራ ቁጥር ሦስት ላይ ያለው ህንፃ የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ኦገስት 2009 ባሳለፈው ውሳኔ ድርጅቱ እ.ኤ.አ. ከ ኦገስት 25 ቀን 2009 እስከ ፌብርዋሪ 24 ቀን 2089 ድረስ ለ80 ዓመት ይዞታውን ከሊዝ ነጻ በሆነ ክፍያ እንዲገለገሉበት ውል ፈጽሟል፡፡
- በተራ ቁጥር አምስት ላይ የተገለፀው ፋብሪካ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬትና የአካባቢ ጥበቃ ቢሮን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 147/2001 መሰረት ከ30/08/2007 ዓ.ም ጀምሮ ለ45 ዓመት በገጠር መሬት ኪራይ እንዲገለገልበት የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል፡፡
- የፋብሪካውን አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ባንኩ በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው ንብረቶች አስተዳደር ክፍል ከሳር ቤት ወደ ቄራ በሚወስደው ዋና መንገድ ከሳልቫቶሪ ዲቬታ የእንጨትና ብረታ ብረት ስራ ጀርባ 50 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ወልደማርያም ህንፃ መዳረሻ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 011 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በአካል በመቅረብ መመልከት ይቻላል፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ በመክፈል ከዿጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቄራ ቅርንጫፍ፣ ወላይታ ዲስትሪክት፣ ድሬዳዋ አብይ ቅርንጫፍ እንዲሁም አዳማ ዲስትሪክት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 25% /ሃያ አምስት በመቶ / የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ለሚቀርብ ተጫራች ባንኩ ባለው የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሠረት ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡት ንብረቶች መካከል የጨርቃ ጨርቅ ማሽነሪዎቹ ከፋብሪካው ተነጥለው አይሸጡም፡፡
- በተራ ቁጥር 6 8 ፣ 10 ፣ 11 እንዲሁም 12 እና 13 ላይ ከተጠቀሱት መኖሪያ ቤቶች በስተቀር በሌሎቹ ንብረቶች ላይ በሽያጭ ገንዘብ ላይ የሚታሰብ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ገዢ ጨምሮ ይከፍላል፡፡
- ተጫራቾች ለንብረቶቹ የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ካሰፈሩ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ መስከረም 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ
- ከተራ.ቁ 1 እስከ ተራ.ቁ 5 ድረስ ላሉት ንብረቶች ከሳር ቤት ወደ ቄራ በሚወስደው ዋና መንገድ ከሳልቫቶሪ ዲቬታ የእንጨትና ብረታ ብረት ስራ ጀርባ 50 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ወልደማርያም ህንፃ ምድር ቤት የቢሮ ቁጥር 004
- ከተራ.ቁ 6 እስከ 9 ላይ ለተጠቀሱት ንብረቶች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
- ከተራ.ቁ 10 እስከ ተራ.ቁ 12 ላይ ለተጠቀሱት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
- ተራ ቁጥር 13 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወላይታ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
- ጨረታው መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ከላይ በተራ ቁጥር አስራ ሁለት ላይ በተገለፁት አድራሻዎች ይከፈታል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113-85-21-39 ወይም 0911 48-29-14 አዲስ አበባ፣ 0912-32-08-54 ድሬደዋ እንዲሁም 0221-11-22-75 እና 0221-11-27-50 አዳማ 0465-80-07-56 ወይም 046-551-35-22 እና 046-554-0311 ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ባንኩ በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው ንብረቶች አስተዳደር ክፍል በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡