የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለፁትን  እና በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው  የተለያዩ ንብረቶችን በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Commercial-Bank-of-Ethiopia-Logo-6

Overview

  • Category : Industry & Factory Foreclosure
  • Posted Date : 07/17/2022
  • Closing Date : 08/16/2022
  • Phone Number : 0113852139
  • Source : Reporter

Description

 የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለፁትን  እና በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው  የተለያዩ ንብረቶችን በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 

ተ.ቁ

 

 

ለጨረታ የቀረበው ሕንፃ/ንብረት አገልግሎት

ቤቱ/ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ 

የቦታው ስፋት ሜ2

 

የካርታ/የባለቤትነት

ማረጋገጫ ሠነድ ቁጥር

 

 

የጨረታ መነሻ ዋጋ

 

 

ከተማወረዳቀበሌየቤት ቁጥር
 

1

የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ህንፃሰበታዲማ117 ሄክታርL/2413/2001657,727,708.05
2የተለያዩ የጨርቃ ጨርቅ ማሽነሪዎችሰበታዲማ1129‚856‚283.40
                                                                                                            ጠቅላላ ድምር787,583,991.45
3 

ለፋብሪካ እና ለቢሮ  አገልግሎት የሚውል በግንባታ ላይ ያለ  ህንፃ

 

ሰበታ

 

ሃዋስ

 

ሃሮ ጂላ ፋልሶ

 33‚430 ሜ.ካ 

WLBEN/6844/BL9

 

83,274,097.62

4መኖሪያ ቤትዋጩ /ም.ሐረርጌ/ሀብሮ 85.5 ካ.ሜ140‚356.96
5ንግድ ቤትገዋኔአፋር 56.82 ካ.ሜ304‚358.66
6ንግድ ቤትድሬዳዋመልካ ጀብዱ4‚800.00
7ወፍጮ ቤትገለምሶ34‚500.00
8መኖሪያ ቤትመተሀራፈንታሌ01018644018/32/1794406‚503.81
9መኖሪያ ቤትጂቱሀሮ01268 ካሬ2248748‚306.43
10ሱቅቆሬሸሬ55 ሜ.ካሬ54‚954.41
11መጋዘንቆሬሸሬ57.6 ሜ.ካሬ57‚552.25
12መኖሪያ ቤትቆሬጎቤ90 ሜ.ካሬ89‚505.68
13የተለያዩ የስካኒያ ተሽከርካሪ  መለዋወጫዎችአዲስ አበባ281‚711.82
14የትምህርት ቤት  ህንፃመተማ ዮሐንስ03/014500 ሜ.ካሬኢን-0116‚900‚000.00

ማሳሰቢያ

  1. የንብረቶቹን አጠቃላይ ሁኔታ በግንባር ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ባንኩ የጉብኝት ፕሮግራም እንደ አስፈላጊነቱ ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡
  2. በተራ ቁጥር አንድ ላይ ያለው ህንፃ የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ኦገስት 2009 ባሳለፈው ውሳኔ ድርጅቱ እ.ኤ.አ. ከ ኦገስት 25 ቀን 2009 እስከ ፌብርዋሪ 24 ቀን 2089 ድረስ ለ80 ዓመት ይዞታውን ከሊዝ ነጻ በሆነ ክፍያ እንዲገለገሉበት ውል ፈጽሟል፡፡
  3. በተራ ቁጥር ሦስት ላይ የተገለፀው ፋብሪካ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬትና የአካባቢ ጥበቃ ቢሮን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 147/2001 መሰረት ከ30/08/2007 ዓ.ም ጀምሮ ለ45 ዓመት በገጠር መሬት ኪራይ እንዲገለገልበት የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል፡፡
  4. የሳይገን ዲማ ፋብሪካን አጠቃላይ ሁኔታን የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ባንኩ በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው ንብረቶች አስተዳደር ክፍል ከሳር ቤት ወደ ቄራ በሚወስደው ዋና መንገድ ከሳልቫቶሪ ዲቬታ የእንጨትና ብረታ ብረት ስራ ጀርባ 50 ሜትር ገባ ብሎ  በሚገኘው  ወልደማርያም  ህንፃ መዳረሻ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 011 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በአካል በመቅረብ መመልከት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ በመክፈል ከሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቄራ ቅርንጫፍ፣ ነቀምት ዲስትሪክት፣ ሻሸመኔ ዲስትሪክት፣ ድሬዳዋ አብይ ቅርንጫፍ ፣ አዳማ ዲስትሪክት  እንዲሁም ጎንደር ዲስትሪክት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 25% /ሃያ አምስት በመቶ / የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ለሚቀርብ ተጫራች ባንኩ ባለው የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሠረት ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
  9. ለጨረታ ከቀረቡት ንብረቶች መካከል የጨርቃ ጨርቅ ማሽነሪዎቹ ከፋብሪካው ተነጥለው አይሸጡም፡፡
  10. በተራ ቁጥር 4፣ 8 ፣  9  እና 12  ላይ  ከተጠቀሱት መኖሪያ ቤቶች በስተቀር በሌሎቹ ንብረቶች ላይ በሽያጭ ገንዘብ ላይ የሚታሰብ 15%  የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ገዢ ጨምሮ ይከፍላል፡፡
  11. ተጫራቾች ለንብረቶቹ የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ካሰፈሩ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ  ነሐሴ 09  ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ
  • ከተራ.ቁ 1 ፣ 2 ፣ 3  እና 13 ላይ ያሉ ንብረቶች  ከሳር ቤት ወደ ቄራ በሚወስደው ዋና መንገድ ከሳልቫቶሪ ዲቬታ የእንጨትና ብረታ ብረት ስራ ጀርባ  50 ሜትር ገባ ብሎ  በሚገኘው  ወልደማርያም  ህንፃ  ምድር ቤት የቢሮ ቁጥር 004
  • ከተራ.ቁ 4 እስከ 7 ላይ ለተጠቀሱት  ንብረቶች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
  • ተራ.ቁ 8 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
  • ተራ ቁጥር 9 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነቀምት ዲስትሪክት ጽ/ቤት
  • ከተራ.ቁ 10 እስከ ተራ.ቁ 12 ላይ ለተጠቀሱት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
  • ተራ.ቁ 14 ላይ ለተጠቀሰው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
  1. ጨረታው ነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት  ከላይ በተራ ቁጥር አስራ አንድ ላይ  በተገለፁት አድራሻዎች  ይከፈታል፡፡
  2. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113-85-21-39 ወይም 0911 48-29-14 አዲስ አበባ፣ 0912-32-08-54 ድሬደዋ ፣ 0221-11-22-75 እና 0221-11-27-50 አዳማ ፣ 057-661-76-73 እና 057-771-09-35  ነቀምት ዲስትሪክት ፣ 046-110-42-72 ሻሸመኔ ዲስትሪክት እና 0581-26-00-47 ጎንደር ዲስትሪክት በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ  ባንኩ በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው ንብረቶች አስተዳደር ክፍል በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  3. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡