የኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን ሲገለገልባቸው የነበሩትን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Sale
- Posted Date : 04/20/2021
- E-mail : eth@mf.worldathletics.org
- Phone Number : 0116479731
- Source : Reporter
- Closing Date : 05/09/2021
Description
የኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን ሲገለገልባቸው የነበሩትን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በአዲስ አበባ ስታዲዮም አጠገብ በሚገኘው ትንሿ ሜዳ (የማሟሟቋያ ሜዳ) ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00–10፡00 መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች ጠቅላላ ዋጋ ሃያ በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የንበረቶቹን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቾቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኢንቨሎፕ /ፖስታ/ በፌደረሽኑ ህንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገበት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ካለ ከጐኑ በተጫራቹ ካልተፈረመ ዋጋ አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት/15/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በአምስት /5/ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካላሆነ ያስየዙት ገንዘብ ለፌዴሬሽኑ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከፌዴሬሽኑ የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ) ብር በመክፈል ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት /15/ የስራ ቀናቶች ውስጥ መግዛት ይችላሉ;;
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት /15/ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በአስራ ስድስተኛው /16/ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ፌዴሬሽኑ ለአሻሻጡ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
Phone Number :011 647 97 31
FAX: 011 645 08 79
E.mail:- eth@mf.worldathletics.org
PO box 13226
ጉርድ ሾላ