የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቀድሞ ብሔራዊ ሆቴል ተብሎ የሚጠራው፣ በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ የነበሩትን የሚወገዱ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ

Ethiopian-Athletics-Federation-የኢትዮጵያ-አትሌቲክስ-ፌዴሬሽን-Logo

Overview

  • Category : Disposal Sale
  • Posted Date : 08/10/2021
  • Phone Number : 0116479794
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 08/21/2021

Description

ነሐሴ 03/2013 ዓ.ም

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቀድሞ ብሔራዊ ሆቴል ተብሎ የሚጠራው፣ በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ የነበሩትን የሚወገዱ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ተከታታይ የሥራ ቀናት መሆኑን እያሳውቅን፤ የጨረታ ተሣታፊዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ተጫራቶች የጨረታውን ማስከበሪያ ቫትን ጨምሮ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፤
  2. ተጫራቶች ጨረታውን ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ጉርድ ሾላ በሚገኘው በድርጅቱ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላሉ፤
  3. ተጫራቶች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 2 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን ቅዳሜ፤ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  5. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡– ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

  ለበለጠ መረጃ፡- 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፋክስ 0116-45-08-79

ፖ.ሳ.ቁ.13336

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን

Send me an email when this category has been updated