የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2015 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የዕቃዎች ግዥ በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Purchases
- Posted Date : 01/10/2023
- Phone Number : 0116479794
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/20/2023
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2015 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የዕቃዎች ግዥ በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የጽሕፈትመሣሪያዎች፤ F የተለያየ መጠን ያላቸው ባነርና መፅሄት
- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፤ F የኤሌክትሮኒክስና ዕቃዎች፣
- የተለያዩ ለህንፃ ጥገና የሚያገለግሉ ዕቃዎች F ፈርኒቸር እና ፊክሲቸር
- የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች F የመኪና ሰርቪስ (አመታዊ ጥገና የሚሰጡ)
- የውድድር ዕቃዎች F የሆቴል አገልግሎት ባለ3ና ባለ4 ኮከብ
- የትራንስፖርት አገልግሎት (45 እስከ 60 ሰው እንዲሁም የራይድ አገልግሎት የሚሰጡ)
በዚሁ መሠረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር የሚያቀርቡትን ዕቃ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሣጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ዕቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው የፍላጎት መግለጫ ዝርዝር መሠረት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ፌዴሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ለበለጠ መረጃ፡- 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ፋክስ 0116-45-08-79 ፖ.ሳ.ቁ 13336
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን