የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚያንቀሳቅሰውን ገንዘብ በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች ተወዳድረው የተሻለ ጥቅማ ጥቅም በሚያቀርብ ባንክ አስቀምጦ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ይፈልጋል፡

Ethiopian-Athletics-Federation-logo

Overview

  • Category : Bank Related
  • Posted Date : 10/15/2022
  • Phone Number : 0116479794
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/28/2022

Description

ጥቅምት 04/2015 ዓ.ም

ግልጽ የባንክ ጨረታ ማታወቂያ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚያንቀሳቅሰውን ገንዘብ በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች ተወዳድረው የተሻለ ጥቅማ ጥቅም በሚያቀርብ ባንክ አስቀምጦ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት  ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የገንዘብ ተቀማጮች በባንክ አስቀምጦ ከዚህ በታች የተገለጹትን ጥቅማ ጥቅም ማግኘት ስለፈለግን፡-

1ኛ. ተንቀሳቃሽ የሀገር ውስጥ ገንዘብ (Local currency) በወለድ ተቀማጭ ለማድረግ የምትሰጡንን የወለድ ምጣኔ መጠኖች

2ኛ. በጊዜ ገደብ (Time Deposit) የሚቀመጥ የሀገር ውስጥ ገንዘብ (Local currency) በስድስት ወራት እና በአንድ ዓመት ቆይታ ተሰልቶና በገንዘብ መጠኑ ተከፋፍሎ የምትሰጡን የወለድ ምጣኔ

3ኛ. ከላይ የተዘረዘሩትን ተቀማጮች በባንካችሁ የሚቀመጥ ከሆነ በሶስት የሀገር ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድሮች ማለት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና፤ በጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ እና በሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድሮች የምትሰጡን ስፖንሰር ሺፕ መጠን

በዚሁ መሠረት ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን ጉርድ ሾላ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ግዥና ፋይናንስ ደጋፊ ሥራ ሂደት ክፍል በብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዳቸውን እስከ አስረኛው ቀን እስከ ረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው በ10ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ስልክ በመደወል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ፌዴሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-  ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

  ለበለጠ መረጃ፡- 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፋክስ 0116-45-08-79

ፖ.ሳ.ቁ.13336

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን