የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የ2013 በጀት ዓመት ደረጃውን የጠበቀ የአትሌት፤ የአሰልጣኝ እና የዳኛ (profile system) በጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Athletics-Federation-የኢትዮጵያ-አትሌቲክስ-ፌዴሬሽን-Logo

Overview

 • Category : Education & Training Services
 • Posted Date : 05/27/2021
 • Phone Number : 0116479358
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/10/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ፤

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የ2013 በጀት ዓመት ደረጃውን የጠበቀ የአትሌት፤ የአሰልጣኝ እና የዳኛ (profile system) በጨረታ አወዳድሮ ማስራት ስለሚፈልግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አሥር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቢሯችን ድረስ መጥታችሁ የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፤ ተመዝጋቢዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

 1. ሕጋዊ አይሲ.ቲ.ሶልሽን ወይም ሶፍትዌር ማጎልበት ፈቃድ ያላቸው ፤
 2. በዘመኑ ሕጋዊ አይሲቲ ሶልሽን ፈቃድ ኦሪጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይገባቸዋል፤
 3. ከዚህ በፊት የተለያዩ ሲስተም በማጎልበት ልምድ የተመሰከረላቸው
 4. በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ሲስተሙን አጎልብቶ ማስረከብ የሚችሉ
 5. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያቁጥር (Tin No.) ያላቸው መሆን አለባቸው፤
 6. ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 5% CPO ማስያዝ አለባቸው፤
 7. የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 50.00 (ሀምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
 8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የአገልግሎት ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመሙላት ማስገባት አለባቸው፤
 9. የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚያኑ ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
 10. ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ፤ ኦሪጂናል፤ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ አሸገው ማስገባት አለባቸው፤
 11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንፃ 2ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

ለበለጠ መረጃ  0116-47-93-58/ 0116-45-08-79/ 0917012504

ደውለው መጠየ ቅይችላሉ፡፡ ወይም

በፋክስ 0116-45-08-79

ፖ.ሳ.ቁ 13336

መላክ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

Send me an email when this category has been updated