የኢትዮጵያ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ማህበር በሆስቴሉ ህንፃ ላይ ለካፌና ሬስቶራንት የሚውል ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : House & Building Rent
  • Posted Date : 07/03/2021
  • Phone Number : 0115572202
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 07/16/2021

Description

የኢትዮጵያ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ማህበር

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን የኢትዮጵያ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ማህበር፣ በሲቪል ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ተመዝግቦ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር ነው፡፡   ማህበራችን ከኤጀንሲው ባገኘው ፈቃድ የገቢ ማስገኛ ድርጅቶችን በስሩ አቋቁሞ እየሰራ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ማህበሩ ስር ካለው ተቋም አንዱ ኢንክሉሲቭ ሆስቴል ነው፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት በሆስቴሉ ህንፃ ላይ ለካፌና ሬስቶራንት የሚውል ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በዘርፉ ልምድና የአገልግሎት ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ በተዘጋጀው የጨረታ  ሰነድ  ላይ  በቀረበው  ዝርዝር  መሠረት  መወዳደር  የምትፈልጉ  ድርጅቶች የጨረታውን ሰነድ ከድርጅታችን በመውሰድ፣ በ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ (እስከ አርብ ሐምሌ 9 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ) 11፡00 ሰዓት የዋጋ ማቅረቢያችሁን በታሸገ ፖስታ በማህበሩ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡   ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ቦሌ ማተሚያ ፊትለፊት፣ በንግድ ባንክና በዳሙ ሆቴል መካከል ወደ ፒኮክ ፓርክ በሚያስገባው ቀጭን አስፋልት መንገድ ገባ ብሎ በስተቀኝ በሚገኘው AEMFI ህንፃ ላይ ፣

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 0115-57 2202

Send me an email when this category has been updated