የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን በአካል ጉዳተኝነት ላይ ያተኮሩ አጫጭር የሬዲዮ ድራማዎችንና ጭውውቶች በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ እንዲተላለፍ ይፈልጋል፡፡

FEAPD-The-Federation-of-Ethiopian-Associations-of-Persons-with-Disabilities-FEAPD-logo-reportertenders-1

Overview

  • Category : Entertainment & Docu
  • Posted Date : 04/17/2021
  • Phone Number : 0111553003
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 04/30/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን በሀገራችን ለ6ኛ ጊዜ በሚካሄደው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ አካል ጉዳተኞች በመራጭነትና በተመራጭነት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና በአካል ጉዳተኝነት ላይ የሚስተዋሉ የግንዛቤ ክፍተቶችን በአካል ጉዳተኝነት ላይ ያተኮሩ አጫጭር የሬዲዮ ድራማዎችንና ጭውውቶች ላይ በቂ ልምድ ያላቸውን የመገናኛ ብዙሃን ወይም በኪነ ጥበብ ስራ የተሰማሩ ድርጅቶችን አወዳድሮ የ1 (አንድ) ሰዓት አጫጭር የሬዲዮ ድራማዎችንና  ጭውውቶችን በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች በክልልና በብሄራዊ ደረጃ ቅርንጫፍ ባላቸው የሬዲዮ ጣቢያዎች እንዲሁም የሁለት ደቂቃ አጭር የቴሌቪዥን መልእክት ተዘጋጅቶ እንዲተላለፍ ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን ህጋዊ ሰነዶች በማሟላት ለተጫራቾች የተዘጋጀውን አጭር የስራ መግለጫ (ToR) ከሚያዚያ 11 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. ጀምሮ ናይጀሪያ ኤንባሲ አካባቢ ከኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ ፊት ለፊት ወደ ችሎት / ጉቶ ሜዳ በሚወስደው መንገድ 8ዐ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በሚገኘው ጽ/ቤታችን ዘወትር በስራ ሰአት በአካል በመቅረብ ሰነዱን ወስዳችሁ እንድትጫረቱ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 – 1553003 / 0913 – 885132 ይደውሉ፡፡