የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን እ.ኤ.አ. የ2021 ሒሳቡን በውጭ ኦዲተሮች ማስመርመር ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ኦዲተሮች መወዳደር ይችላሉ፡፡

FEAPD-The-Federation-of-Ethiopian-Associations-of-Persons-with-Disabilities-FEAPD-logo-reportertenders

Overview

  • Category : Auditing Related
  • Posted Date : 11/10/2021
  • Phone Number : 0910371055
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/16/2021

Description

የሒሳብ ምርመራ ጨረታ ማስታወቂያ

 የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን እ.ኤ.አ. የ2021 ሒሳቡን በውጭ ኦዲተሮች ማስመርመር ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ኦዲተሮች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  • ሥራውን ለመሥራት የሚያስችል የታደሰ ንግድ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው፣
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • በኢትዮጵያ ውስጥ ለመሥራት የተመዘገቡ፣
  • መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሒሳብ ምርመራ ልምድ ቢኖራቸው ይመረጣል፣

በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 20 የሰነድ ፋይሎች /Box file/ ለመመርመር የሚሠሩበትን ዋጋ እና ሥራው የሚፈጅባቸውን ጊዜ በመጥቀስ የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከሰሜን ሆቴል ጀርባ ወደ ናይጄሪያ ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ መግቢያ በር ፊት ለፊት በሚገነጠለው አስፋልት ከ6ዐ – 70 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው መ/ቤታችን የሰው ሀብትና ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ

በስልክ ቁጥር 0910 – 37 10 55 / 011 – 155 30 03 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡