የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ በታች የተገለጹትን የጽህፈት መሳሪያዎች የጽዳት ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Stationery Supplies
 • Posted Date : 07/20/2022
 • Phone Number : 0115158284
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/28/2022

Description

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የጨረታ ማስታወቂያ 

ፌዴሬሽናችን ከዚህ በታች የተገለጹትን የጽህፈት መሳሪያዎች የጽዳት ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት የጨረታ ሰነድ በየዕቃዎቹ ዓይነት ማለትም፡-

ተ.ቁ የዕቃው አይነት ምድብ
1 የጽህፈት መሣሪያ ሎት 1
2 የፅዳት ዕቃዎች ሎት 2
3 የደንብ ልብስ ጨርቅ፣ ሸሚዝ፣ ጫማ(ጉርድ የወንድና የሴት) ፣ ካፖርት፣ የዝናብ ልብስ፣ የሽርጥ ጨርቅ(ካኪ)፣ የውስጥ ልብስ ጨርቅ፣ ካኪ ቱታ እና ቦቲ ጫማ ሎት 3

 የተዘጋጁ ሲሆን

 1. ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የተጨመሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ ማስረጃ የማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በፌዴሬሽኑ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች ስለጨረታው የሚገልፀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር የቀድመው አይቤክስ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ እና ቴክኒካል ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ እስከ ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 6. ፌዴሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አድራሻ ወሎ ሰፈር ኢትዮ ቻይና መንገድ

የቀድሞው አይቤክስ ሆቴል ፊት ለፊት

ስ.ቁ 0115 158284

አዲስ አበባ