የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ድርጅት ልዩ ልዩ የኦዲዮ ቪዥዋል ዕቃዎችና የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ኮምፒተሮች፣ ዘመናዊ ቪዲዮ ካሜራዎች፣ የካሜራዎች መብራቶች ወዘተ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Tewahido-Church-logo-Reportertenders

Overview

 • Category : Electrical Equipment & Accessories
 • Posted Date : 09/04/2021
 • Phone Number : 0118121224
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/14/2021

Description

የጨረታ ግዥ  ማስታወቂያ

     የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ድርጅት ልዩ ልዩ የኦዲዮ ቪዥዋል ዕቃዎችና የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ኮምፒተሮች፣ ዘመናዊ ቪዲዮ ካሜራዎች፣ የካሜራዎች መብራቶች ወዘተ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡  በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ

 1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የመንግሥት ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
 2. ዕቃዎቹን ከድርጅቱ ጽ/ቤት ድረስ አምጥተው ትክክለኛነታቸው በድርጅቱ የጥራትና ቴክኒክ ባለሙያዎች ሲረጋገጥ ገጣጥመው ማስረከብ የሚችሉ
 3. በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፀው የዕቃዎች ጥራትና ዓይነት መስፈርት (ስፔስፊኬሽን) መሠረት የሚያስረክቡና ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎቹ ጥራትና ብቃት በቂ ዋስትና መስጠጥ የሚችሉ
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የተወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በድርጅቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ እና CPOውንም ከዚህ ጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. አሸናፊው ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ከዋጋው ላይ የሚታሰብለት ሲሆን ተሸናፊዎች ያስያዙት  CPO ይመለስላቸዋል፡፡
 6. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 ብር (ሦስት መቶ ብር) ከድርጅቱ በመግዛት ሰነዱ በሚጠይቀው መሠረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7(ሰባት) የሥራ ቀናት ዘወትር በመንግሥት የሥራ ሰዓት 5 ኪሎ ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ7ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣዩ የመንግስት መ/ቤቶች የሥራ ቀን  ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ጽ/ቤት (አዳራሽ) ይከፈታል፡፡ የጨረታው አሸናፊ በማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
 7. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ዕቃዎቹን አስረክቦ ማጠናቀቅ አለበት፡፡
 8. ስለሚገዙት እቃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተጠቀሰው ውጪ ዝርዝር እና ስዕላዊ መግለጫ ለማግኘት በEOTC Tv በቴሌግራምና በፌስ ቡክ ገጻችን መመልከት ይችላሉ፡፡
 9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ድራሻ፡- 5 ኪሎ ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ድርጅት

ለበለጠ መረጃ  ስልክ.ቁ፡- 0118-121224/21 – 0911-03-50-87