የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከጅቡቲ ወደብ በውርስ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባቸውን Reinforcing deformed steel bars and Prime steel square billets ብረቶች በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ethiopia-shipping-logo

Overview

 • Category : Steels & Aluminium supply & sale
 • Posted Date : 07/11/2022
 • Phone Number : 0115549257
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/20/2022

Description

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ሐጅ/09/2014

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከጅቡቲ ወደብ በውርስ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባቸውን Reinforcing deformed steel bars and Prime steel square billets ብረቶች በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተመለከተውን መመዘኛ መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በሀራጅ ሽያጩ ላይ መጫረት ይችላል፡፡

 1. በሐራጅ ሽያጭ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፈቃድ ያለው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የምስክር ወረቀት እንዲሁም የግብር መለያ ቁጥር የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡
 2. የሐራጅ ጨረታው ንብረቱ በሚገኝበት በቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት ይካሄዳል፡፡
 3. የሐራጅ ጨረታው በተቀመጠለት ሰዓት ውስጥ ካልተጠናቀቀ ላልተወሰነ ጊዜ ሊራዘም ይችላል፡፡
 4. የሐራጅ ጨረታ ሽያጭ የሚሳተፉ ተጫራቾች ጨረታው ከመጀመሩ በፊት ተመዝግበው ለሚወዳደሩበት የማስጫኛ ሰነድ(bill of loading) ቁጥር ስር ለሚገኙ ብረቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በC.P.O ብቻ የመነሻ ዋጋውን 20%(ሃያ በመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
 5. ለተሸናፊዎች ያስያዙት ዋስትና በ3/ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊው ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡
 6. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5/አምሰት/ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዕቃ ዋጋ ለድርጅቱ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የጨረታው አሸናፊ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ገቢ ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
 7. አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ባደረገ በ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡
 8. በጨረታው የተሸጠ ዕቃ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካልተነሳ ኪራዩ በደረቅ ወደብ አገልግሎት ታሪፍ መሰረት ሆኖ ዕቃው ከተሸጠበት ከ20ኛው ቀን ጀምሮ የገዛው ሰው እስከሚረከበው ድረስ የቆየበት ጊዜ ይሆናል፡፡
 9. ማንኛውም ተጫራች መጫረት የሚችለው በማስጫኛ ሰነድ(bill of loading) ቁጥር ስር የተመለከቱትን ሁሉንም ብረቶች በአንድ ላይ ሲሆን ነጥሎ መወዳደር አይችልም፡፡
 10. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበውን የንብረት ዝርዝር እና የጨረታ መነሻ ዋጋ በዋናው መ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የተለጠፈ ሲሆን ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት ማየት ይችላሉ፡፡
 11. የናሙና ዕይታ፣ የC.P.O ማስገቢያ እና የሐራጅ ሽያጭ መርሀ ግብር ከስር በተገለፀው መሰረት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የዕቃው ዓይነት የናሙና ዕይታ እና C.P.O ማስገቢያ ቀንና ሰዓት የሐራጅ ጨረታው የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት
1. Reinforcing deformed

steel bars

2. Prime steel square

billets

·     ሐምሌ 13/2014 ዓ.ም

·     ጠዋት ከ3፡00-6፡00 ሰዓት

·     ከሰዓት ከ8፡00-11፡00 ሰዓት

·     የጨረታው ቀን በ14/11/2014 ዓ.ም

ጨረታው የሚጀመርበት ሰዓት

·     ጠዋት ከ3፡00-6፡00 ሰዓት

·     ከሰዓት ከ8፡00-11፡00 ሰዓት

ማሳሰቢያ፡-

የናሙና ዕይታ እና C.P.O ማስገቢያ ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ብቻ የምናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት
 1. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549257/0115549478 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡