የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከታች በዝርዝር የተገለጹትን ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች እና ማባዣ ማሽኖች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Chamber-of-Commerce-and-Sectoral-Association-ECCSA-logo

Overview

 • Category : Computer Purchase
 • Posted Date : 08/27/2022
 • Phone Number : 0115514005
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/10/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከታች በዝርዝር የተገለጹትን ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች እና ማባዣ ማሽኖች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የእቃው አይነት መለኪያ ብዛት
1 ላፕቶት በቁጥር 30
2 ፕሪንተር በቁጥር 4
3 ማባዣ/ኮፒየር በቁጥር 2

ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ም/ቤቱ ይጋብዛል፡፡

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ/ክሊራንስ/ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ከ 2፡30 እስከ 10፡00 ዝርዝር የግዢ ሰነዱን/ SPECIFICATION ሜክሲኮ በሚገኘው የምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 05 በመውሰድ ፋይናንሻል ፕሮፖዛል እስከ ቋግሜ 04 ባሉት ቀናቶች ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ለእያንዳንዱ የእቃ ግዢ፣ በተመሳሳይ የእቃ ግዢ አይነት አጠቃላይ ድምር እና የሁሉንም ግዢዎች ድምር ቫትን ጨምሮ በግልጽ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት በግርጌው ስም፣ ፊርማ እና የድርጅታችሁን ማህተም በማኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው መስከረም 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በም/ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ ይከፈታል፡፡
 6. የጨረታ አሸናፊ በም/ቤቱ የማስታወቂያ ቦርድ ይለጠፋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ም/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር  251-11-5514005 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡