የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትበሽመና ዘርፍ ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የሚጠቀሙበት የተለያዩ አይነት ያላቸውን የዘሃ ክር አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Industrial-Inputs-Development-Enterprise-Logo-2

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 11/14/2022
 • Phone Number : 0113692243
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/29/2022

Description

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

የኢንዱስትሪ ግብዓት ግዥ ዳይሬክቶሬት

የዘሃ ክር ግዥ ግልጽ ጨረታ

(ቁጥር ኢኢግልድ/05/2015)

የጨረታ ማስታወቂያ፡-

ድርጅታችን በሽመና ዘርፍ ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የሚጠቀሙበት የተለያዩ አይነት ያላቸውን የዘሃ ክር አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ አምራቾች/አቅራቢዎች፣

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የዘሃ ክር ወካይ ናሙና ከየአይነቱ አንድ አንዳንድ ኮን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ በተለምዶ ቢስ መብራት (አትክልት ተራ) በሚባለው አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሰነዶች ጋር በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ ለየብቻው በፖስታ በማሸግ እስከ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 6. ጨረታው ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ  የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113-69-22-43/0113-69-18-86

www.eiide@eiide.com.et