የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የጉምሩክ ማስተላለፍ /Custom Clearing/ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማሰታወቂያ

Ethiopian-Industrial-Inputs-Development-Enterprise-Logo

Overview

 • Category : Labor Supply Service
 • Posted Date : 01/21/2023
 • Phone Number : 0113690791
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 02/02/2023

Description

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

የጉምሩክ ማስተላለፍ /Custom Clearing/ አገልግሎት ግዥ

የጨረታ ማሰታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 011/15

ድርጅታችን ከውጭ ሀገር በቦሌ አየር መንገድ በካርጎ ትራንስፖርት ለሚያስመጣቸው የሽያጭ መመዝገቢያና መለዋወጫ ዕቃዎች የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓትን ለማስፈፀም እንዲቻል በአየር ትራንስፖርት ጉምሩክ አስተላላፊ /Custom Clearing Agent/ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በረዥም ጊዜ ኮንትራት መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆንም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መካፈል የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ሚያሳይ ከእዳ ነፃ ደብዳቤ የሙያ እና ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 2. ለዚህ ጨረታ ሲባል የተዘጋጀውን ሰነድ በማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ፒያሳ ቢስ መብራት አካባቢ /አትክልት ተራ/ የኢንዱስትሪ ውጤቶች የውጭ ሀገር ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ` ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 4. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው በተመሳሳይ ቀንና (ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም) ከረፋዱ 4፡10 ተጫራቾች ወይም ወኪሎች በተገኙበት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
 6. ተጫራቾች ከዚህ ማስታወቂያ በተጨማሪ በጨረታው መመሪያ ላይ የቀረቡትን ደንቦች በሙሉ የመፈፀም ግዴታ አለባቸው፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ አልያም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

ስልክ ቁጥር 0113-69-07-91/0113-69-27-11

www.eiide.com.et