የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (EVA) የኮሮና በሽታን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎችን የሚያሟሉ ባለ ሶስት (3) ኮከብ እና ከዚያ በላይ ደረጃ ያላቸው ሆቴሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለማግኘት ይፈልጋል።

Overview

 • Category : Hotel & Ticket Service
 • Posted Date : 07/24/2022
 • Phone Number : 0115525020
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/03/2022

Description

የሆቴል አገልግሎት ለማግኘት የወጣ አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (EVA) ከአውሮፓ ሕብረት (EU) ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሶስት ብሔራዊ ክልሎች (አማራ፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ) የእንስሳት ሀብት ልማት ፕሮግራሞችን ለማጎልበትና የዘርፉን ምርታማነት ይበልጥ ለማሻሻል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

ማኅበሩ የእንስሳት ልማት ሥራዎችን ለማስፋፋትና ጠቃሚ ልምዶችንና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስተዋወቅ የሚያስችል 35ኛ ጠቅላላ ዓመታዊ ኮንፈረንስ በነሐሴ 24 እና 25 ቀን 2014 ዓ.ም ለማካሄድ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ሲሆን፤ ኮንፈረንሱን ለማሰናዳት አቅም ያላቸው፣ የኮሮና በሽታን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎችን የሚያሟሉ ባለ ሶስት (3) ኮከብ እና ከዚያ በላይ ደረጃ ያላቸው ሆቴሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለማግኘት ይፈልጋል። በዚሁም መሠረት የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ሆቴሎች እንዲወዳደሩ በአክብሮት ይጋብዛል፡-

 1. የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርነት ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 3. ሆቴሉ ባለ ሶስት (3) ኮከብ ወይም ከዚያ በላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ የሚያቀርቡ፤
 4. የCOVID-19 ፕሮቶኮልን ተመርኩዞ በአንድ ጊዜ ቢያንስ 500 ተሳታፊዎችን (“Half-Moon ወይም Classroom seat Arrangement”) ማስተናገድ የሚችል አዳራሽ ያላቸው ሆኖ፤
  • ኮንፈረንሱን በአካል (Physical) እና በይነ-መረብ (Virtual) ማስተናገድ የሚችል ፈጣንና አስተማማኝ የኢንተርኔት፣ ኦዲዮ ቪዥዋል፣ LCD projector እና ስክሪን አገልግሎት ያለው፤
 • አዳራሹ ያለምንም የድምጽ ብክለት ስብሰባውን ማካሄድ የሚያስችል መሆኑን፤
 • ምርቶችንና አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ፣ እያንዳንዳቸው 6ካሜ ስፋት ኖሮአቸው ቢያንስ 20 ድርጅቶችን ማስተናገድ የሚችሉ የኤግዚቢዥን ቦታዎች በኮንፈረንሱ አዳራሽ አቅራቢያ ማመቻቸት የሚችል፤
 • የኮንፈረንሱን ተሳታፊዎች ለማስተናገድ የሚችል የሬስቶራንትና ካፍቴሪያ አገልግሎት ያላቸው፤ እንዲሁም በቂ የተሸከርካሪዎች ማቆሚያ ቦታ ያላቸው፤
 • የኮንፈረንሱን ታዳሚዎችን ለመመዝገብና የሕትመት ውጤቶችን ለማሠራጨት የሚውል በቂ ቦታ ማዘጋጀት የሚችል፤
 1. ድርጅትዎ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተዘረዘሩ መሥፈርቶችን የሚያሟላ ከሆነ፤ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ ቀናት ከማኅበሩ (EVA) ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 303/306 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2:30 እስከ 10:30 ድረስ ቀርበው የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
 2. ተጫራቾች ማህበሩ ባቀረበው የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸውን ዝርዝር (Specification) መሠረት በማድረግ ዋጋቸውን በድርጅቱ (በሆቴሉ) የፕሮፎርማ ማቅረቢያ ላይ ከVAT በፊት እና ከVAT በኋላ በግልጽ ሞልተው በኤንቨሎፕ በማሸግ ማሕበሩ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፣ ጨረታውን ያላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ አሸናፊ ድርጅት እንደተለየ ወዲያኑ ይመለስላቸዋል።
 4. ጨረታው በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። ሆኖም የተጫራቾች ወይም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
 5. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር +251-115-525-020፣ 09-11-18-05-33፣ 09-60-03-71-25፣ 09-52-67-77-94 ወይም 09-40-08-61-94 ደውሎ ዝርዝር መረጃ መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፦ ከእንግሊዝ ኢምባሲ (British Embassy) ፊት ለፊት 600 ሜትር ገባ ብሎ ወደ School of Tomorrow በሚወስደው መንገድ፣ ይመናሹ ሕንጻ አጠገብ እንገኛለን፡፡

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር