የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን መለያ ምልክት አርማ ወይም ሎጎ በመቀየር በአዲስ መልክ እንዲሰራለት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Graphic Designs & Printing
 • Posted Date : 10/15/2022
 • Phone Number : 0911307460
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/21/2022

Description

የሎጎ ዲዛይን ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን መለያ ምልክት አርማ ወይም ሎጎ በመቀየር በአዲስ መልክ እንዲሰራለት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ስራ ዘርፍ በቂ ልምድና እውቀት ያላቸው ድርጅቶች፣ ተቋማት ወይም ግለሰቦች እንዲሳተፉ ማህበሩ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

በዚህ ጨረታ የሚሳተፉ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡   

 1. ድርጅቱ፣ ተቋሙ ወይም ግለሰቡ ከዚህ በፊት ሰፊ ልምድና ተሞክሮ ያለው ስለመሆኑ ለዚህም ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 3. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማህበሩ ፅ/ቤት በሚገኝበት አድራሻ በግንባር በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 05 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ የውድድር ሰነዳቸውን ለማህበሩ ፅ/ቤት ያቀርባሉ፡፡
 6. ጨረታው ህጋዊ ተወካዮች ወይም ተጫራቾች በተገኙበት ማህበሩ በውስጥ ማስታወቂያ በሚገልፀው ቦታ እና ቀን ይከፈታል፡፡
 7. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

አድራሻ፡- ደምበል አደባባይ ከደምብል ሲቲ ሴንተር ጀርባ በሚገኘው አድማስ ዩኒቨርሲቲ ዋና መስሪያቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203

ለበለጠ መረጃ፡– 0911307460/0944352939 መደወል ይችላሉ፡፡ 

ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ለመጫረት ፍላጎት ያለው በተጠቀሱት ቀናት ደምበል አካባቢ በሚገኘው ቢሯችን ድረስ በመቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ እና የንድፈ ኃሳብ አጭር መግለጫ ሰነድ መውሰድ ይኖርበታል፡፡