የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ የሚገኙትን ያገለገሉ ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Agricutural-Transformation-Agency-logo

Overview

  • Category : Tyre & Battery
  • Posted Date : 04/23/2021
  • Phone Number : 0114432018
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 05/14/2021

Description

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ የሚገኙትን ያገለገሉ ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መሠረት ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

1

ያገለገሉ አነስተኛ እና ትላልቅ ጎማዎች፣ ከመነዳሪዎችና ፍላፖች

2

ያገለገሉ ባትሪዎች

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

ሀ) ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ስዓት የጨረታ ሰነዱ በሚገኝበት በአዲስ አበባ በተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ በመቅረብ የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

ለ) የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአዲስ አበባ በዘርፉ ጽ/ቤት  ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡ ጨረታውም በ15 ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ስዓት ተዘግቶ ጧት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ  አዲስ አበባ ይከፈታል፡፡

ሐ) ያገለገሉ አነስተኛ እና ትላልቅ ጎማዎች፣ ከመነዳሪዎችና ፍላፖች እና ያገለገሉ ባትሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (የተሸከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ) ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

መ) ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ በፊት በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ በዝርዝር በማመላከት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-የቃሊቲ ጉምሩክ ፊትለፊት የቃሊቲ ባቡር የመጨረሻ ጣቢያ አዋሽ ባንክ ያለበት ህንፃ በስተጀርባ የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ህንፃ ያለበት ግቢ የተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 12

ስልክ ቁጥር፡- 0114-43-20-18

           0114-70-84-70

               0114-42-5637