የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. ለዋና ቢሮ የሚገለገልበት እና/ወይም ለኪራይ/ለንግድ/ የሚውል ደረጃውን የጠበቀ ህንፃ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 12/24/2022
 • Phone Number : 0115575757
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/18/2023

Description

    የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን .          

የህንፃ ግዥ ጨረታ

 የጨረታ ቁጥር፡ 0001/2015

 1. የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. ለዋና ቢሮ የሚገለገልበት እና/ወይም ለኪራይ/ለንግድ/ የሚውል ደረጃውን የጠበቀ ህንፃ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
 2. ስለሆነም ፍላጎት ያላቸው የሕንፃ ባለቤቶች በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች እና ሰነዶች በማሟላት በኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለ ክፍያ በመውሰድ በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
 3. የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. ሊገዛ የሚፈልገው ሕንፃ፡
 • ለቢሮ አገልግሎት ምቹ ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከዋና መንገድ ዳር ወይም ከዋና መንገድ ብዙ ያልራቀ /Prime Location/፤
 • የሕንፃው ዓይነት፡ ለቢሮ ፣ ለንግድ ወይም ለቅይጥ አገልግሎት መዋል የሚችል፤
 • ሕንፃው የሚገኝበት የግቢ ስፋት ከ400 ካሬ ያላነሰ፡ ጠቅላላ የመጠቀሚያ ወለል ስፋት (መተላለፊያን፣ ደረጃን እና መታጠቢያ ቤትን ወ.ዘ.ተ. ሳይጨምር) ከ2,000 ካሬ ሜትር የማያንስ፤
 • የመኪና ማቆሚያ፡ ቢያንስ 20 መኪኖች በቦታው ግቢ ውስጥ ማቆም የሚችል
 • የሕንፃው ያለበት የግንባታ ደረጃ፡ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ
 • በተጨማሪም ሊፍት፣ ጀነሬተር፣ ራይዘር፣ የውሃ ታንከር፣ የእሳት አደጋ መከላለከያ፣ የአደጋ ጊዜ መውጫ እና ሦስት ፌዝ የኤሌትሪክ መስመር ያለው፤
 1. ይህ የሕንፃ ግዢ ጨረታ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ሰኞ 8፡30 ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
 2. ተጫራቾች የቴክኒክ መወዳደሪያ ሀሳብና የፋይናንስ ዋጋ ግምገማ ሰነድ በታሸገ ፖስታ በሚከተለው አድራሻ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስታወቂያ ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ

የሰው ሃብትና ተቋም አገልግሎት

ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ፤ ቢትወደድ ባህሩ አብርሃም ህንፃ 6ኛ ፎቅ

ቦሌ መንገድ ደንበል አካባቢ

ስልክ፡ +251-115 57 57 57 ወይም +251 913 03 51 68

ፋክስ፡ +251 11 57 57 58

ኢ-ሜይል ፡ [email protected]

አዲስ አበባ፤ኢትዮጵያ

 1. የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን .