የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በጥናት የተደገፈ ድርጅታዊ መዋቅርና ዕርከን፣ የሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማ-ጥቅም በአማካሪ ድርጅት አስጠንቶ ተግባራዊ ማድረግ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Sports-Federation-Logo-reportertenders

Overview

  • Category : Legal Consultancy
  • Posted Date : 04/17/2021
  • Phone Number : 0911670731
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 04/30/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EPL/003/26/4/21

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር፣ በሊግ ማህበሩ ክለቦች መካከል የሚደረገው የእግር ኳስ ውድድር ለማዘመን የበኩሉን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ማህበሩ የተቋቋመበት ዓላማ ለማሳካት የተለያዩ ባለሙያዎች በመቅጠርና አደረጃጀቱን በማጠናከር ላይ ይገኛል፡፡ ማህበሩ በጥናት የተደገፈ ድርጅታዊ መዋቅርና ዕርከን፣ የሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማ-ጥቅም በአማካሪ ድርጅት አስጠንቶ ተግባራዊ ማድረግ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟላ ማነኛም በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያለው አማካሪ ድርጅት ከዚህ በታች የቀረቡትን የጨረታ መመሪያ እና በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የተመለከቱትን መመዘኛ የሚያሟላ ማነኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች መወዳደር ይችላል፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፐ.ኦ / / ብር       /     /      በማሰራት በድርጅታችን ትክክለኛ ስም (የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር)  ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርማቸዋል፡፡
  1. የጨረታውን ሰነድ በወቅቱ በመሙላት የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ከመጠናቀቁ በፊት ያላቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  2. የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል አዲስ አበባ ስታድየም ውስጥ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ሰነድ ጨረታው በሪፖርትር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እና የጨረታ ሳጥን እስከሚታሸግበት 11ኛው ቀን ድረስ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት አዲስ አበባ ስታድየም ውስጥ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመቅረብ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ድርጅቱ ጨረታውን ከመክፈት አይታገድም፡፡
  4. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 07፣ አዲስ አበባ ስታድየም ውስጥ 1ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ 0911 67 07 31 ወይም 0916 02 36 88 መደወል ይችላሉ፡፡