የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በ2013 ዓ.ም የኮከብ ተጨዋች ምርጫ ለማካሄድ የጽሑፍ መልዕክት /SMS Service/ መቀበያ ያለው ድርጅት ሁኖ በተመሳሳይ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማራ እና ከዚህ ቀደም ልምድ ያለው ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ በጋራ መስራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Sports-Federation-Logo-reportertenders-1

Overview

  • Category : Software purch. & Dev. Service
  • Posted Date : 04/19/2021
  • Phone Number : 0916023688
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 04/29/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EPL/003/10/8/13

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በ2013 ዓ.ም እያወዳደረ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር ላይ ተሳታፊ ከሆኑት ቡድን ተጨዋቾች መካከል የዓመቱ ኮከብ ተጨዋች በአጭር የፅሑፍ መልእክት /SMS/ አወዳድሮ ለመምረጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከአክሲዮን ማህበሩ ጋር በመሆን የኮከብ ተጨዋች ምርጫ ለማካሄድ የጽሑፍ መልዕክት /SMS Service/ መቀበያ ያለው ድርጅት ሁኖ በተመሳሳይ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማራ እና ከዚህ ቀደም ልምድ ያለው ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ በጋራ መስራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ድርጅት ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ፕሮፖዛል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ስታድየም በሚገኘው የአክሲዮን ማህበሩ ፅህፈት ቤት የጨረታ ሠነዱን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡  

ጨረታው በ11 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 ላይ በአዲሰ አበባ ስታዲየም የድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጨራቾች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ድርጅቱ ጨረታውን ከመክፈት አይታገድም፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለባቸው፣ ግልጽነት የጎደላቸውና ያልተሟሉ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 07፣ አዲስ አበባ ስታዲየም ውስጥ

ለበለጠ መረጃ 0916 02 36 88 መደወል ይችላሉ፡፡