የኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ በስሩ በሚተዳደሩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የተከማቹ የተለያዩ ያገለገሉ የተሸከርካሪና የማሽን ጎማዎች በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል::

Ethio-Enginering-Group-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Disposal Sale
 • Posted Date : 03/21/2021
 • Phone Number : 0114424441
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/03/2021

Description

ክፍል 1

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ኢ/ኢግ/ን/አ/ኮ/003G/2013

የኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ (ኢ.ኢ.ግ) በስሩ በሚተዳደሩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የተከማቹ የተለያዩ ያገለገሉ የተሸከርካሪና የማሽን ጎማዎች በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

 1. በጨረታውየሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው፣ በዘርፉ የተሰማሩበት የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በዘመኑ የታደሰ ስለ መሆኑ ማረጋገጫ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችሉ፣
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችሉ፣
 3. የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችሉ፣
 4. የተቋሙን ቃለ መሃላ ፎርም አሟልቶ በመፈረም ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችል፣
 5. ለጨረታየሚያስፈልጉ ቅጾችን የሚገኙበት አድራሻ፡

/

የሎት ማጣቀሻ

የንብረቶች ዓይነትና ሰነዱ የሚገኝበት አድራሻ

1

ሎት 01

የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪና የማሽን ጎማዎች መለዋወጫ፣
ዋና መ/ቤት (ንፋስ ስልክና ሞጆ)፣ ብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ (ሳሪስ)፣ ፓወር ኢንጅነሪንግ ኢንዱትሪ (ለቡ መብራት ኃይል)፣ ኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ (ገርጂ)

ከዚህ በላይ በቀረበው ዝርዝር መሠረት በግንባር ቀርበው ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ከዚህ በታች በተመለከተው መሠረት የማይመለስ ብር በመክፈል በመግዛት ማግኘት ይችላሉ፤

 • ሎት 01 የተለያዩ ያገለገሉ የተሸከርካሪና የማሽን ጎማዎች በብር 00
 1. ተጫራቾችየተጠቀሱትን ሰነዶች በመግዛት ማስታወቂያው ከወጣበት መጋቢት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ከሰነዱ ላይ በተጠቀሱት ተቋማት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
 2. ንብረቶቹን ለማጓጓዝ፣ ለጭነት፣ ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች በገዥው ይሸፈናል፣
 3. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ለሎት የተቀመጠውን የጨረታ መነሻ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡ በሎት የተቀመጠውን የመነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) ያልያስያዘና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ወዲያውኑ ውድቅ ይደረጋል፡፡
 5. ጨረታው መጋቢት 25 ቀን2013 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱን በገዙበት ተቋም በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
 6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለተቋሙ ገቢ ይደረጋል፣
 7. ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፑ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
 8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቱን በሚደረግ የውል ስምምነት መሠረት የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
 9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በቀጥታ መስመር ስልክ ቁጥር0114424441 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
 10. ተቋሙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ በህግ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

 

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ

ኢትዮኢንጅነሪንግ ግሩፕ

 

Send me an email when this category has been updated