የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የሐራጅ ሽያጭ (አክሲዮን) ማስታወቂያ

Overview

  • Category : Share Foreclosure
  • Posted Date : 03/28/2021
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 04/07/2021

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር እና በፍ/ባለዕዳ ታምራት ላይኔ (4 ሰዎች) መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 55298 ቀን 21/11/2006 ዓ.ም አና በመ/ቁ 55298 በ13/2013 ዓ/ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አ.ማ. ውስጥ ያላቸው ድርሻ 32624 ሲሆን አንድ አክሲዮን ዋጋ 1784 ሆኖ 1784*32624=58,201.216 የፍ/ባለዕዳ አቶ ንጉሴ ሐይሉ በኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ የሆነ አክሲዮን የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 58,201.216 (ሀምሳ ስምንት ሚሊዮን ሁለት መቶ አንድ ሺ ሁለት መቶ አስራ ስድስት ብር) ሆኖ እዳ እና እገዳ ከሀራጅ ሽያጭ ከተከናወነ በኋላ የሚፈፀም ሆኖ ተጠቃቃሽ መዝገቦች ያሉበት ሆኖ መሆኑ ታውቆ ለመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ/ም0 በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቁ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጐብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት ¼ ኛውን በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡  

Send me an email when this category has been updated