የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት 13 ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡

-ኅብረት-ሥራ-ባንክ-2

Overview

  • Category : Bank Related
  • Posted Date : 01/02/2021
  • Phone Number : 0115576174
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/30/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት 13 ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. የተሸከርካሪዎቹ ዓይነትና ዝርዝር  ሁኔታ በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ እስከ ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ  ቦሌ መንገድ ጌት ሃውስ ህንፃ  የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ ሂሳብ ቁጥር ETB 1446500010001 ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ተሸከርካሪዎች  ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 (ብር ሁለት መቶ) ገቢ በማድረግና ደረሰኙን በመያዝ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ  ዘወትር በሥራ ሰዓት ከባንኩ ንብረት አስተዳደር  ቢሮ ደምበል ህንፃ ምድር ቤት ቢሮ ቁጥር  BMS 01B  መዉሰድ ይችላሉ፤

2. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ የተሸከርካሪዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ብሄራዊ ቴያትር አካባቢ የአዋሽ ባንክ ዋና መ/ቤት ጀርባ በሚገኘው የባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ  በመገኘት ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ፣ ጥር 13 እና ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም  ከጧቱ 4 ሰዓት እከከ 10፡00 ሠዓት መጎብኘት ይችላሉ፤

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ያገለገለ ተሸከርካሪ ዓይነቱንና የሠሌዳ ቁጥር በትክክል በመጥቀስ የሚገዙበትን ዋጋ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት የባንኩ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር BMS 01B በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ያገለገለ ተሸከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋዉን  25% (ሃያ አምስት በመቶ)  በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤

5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% ጋር መሆን አለመሆኑን በግልፅ በሰነዱ ላይ በፅሁፍ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤

6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያልተያያዘለት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ከዉድድር ዉጪም ይሆናል፤

7. ጨረታው ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም  በ10፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ደምበል ሲቲ ሴንተር በ6ኛው አሳንሰር 4ኛ ፎቅ  ግዥ እና ፋሲሊቲ አስተዳደር ቢሮ የሚከፈት ሲሆን፤ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሲባል ተጫራቾች ባልተገኙበት ይከፈታል፤

8. የጨረታዉ ዝርዝር ዉጤት በባንኩ የሺያጭ ኮሚቴ እንደፀደቀ ለተጫራቾች ይገለፃል፤

9. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘዉ ገንዘብ ለተሸናፊ ተጫራቾች ወዲያዉኑ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊ ተጫራቾች ግን ላሸነፉበት ተሸከርካሪ ሙሉ ክፍያዉን ከፍለዉ ንብረቱን ካነሱ በኋላ ተመላሽ ይሆንላቸዋል፤

10 .ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፤

11.አሸናፊ ተጫራቾች ላሸነፉበት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች  በፅሁፍ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያዉን በመፈፀም ንብረቱን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልተከፈለ የጨረታ ማስከበሪያዉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤

12. አሸናፊ ተጫራቾች ላሸነፉበት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች  ክፍያ በመፈፀም ንብረቱን በተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ካላነሱ ባንኩ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ ለቆየበት ብር 300.00 ለሃያ ቀን የምናስከፍል ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካላነሱ ባንኩ በህግ አግባብ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል፤

13.ለጨረታ  የቀረቡት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች  ላይ የሚፈለግ ማንኛዉም ዓይነት የስም ማዛወሪያ፤ ለመንግስት የሚከፈሉ የታክስ ክፍያዎችንና  ሌሎች ወጪዎችን የጨረታ አሸናፊዉ ይከፍላል፤

  1. 14.ባንኩ የተሸለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)

ስልክ ቁጥር 0115576174

ፖ.ሣ.ቁ 16936

Send me an email when this category has been updated