የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ያገለገሉ የቢሮ ወንበር እና ጠረጴዛዎች፣ ኮምፒውተሮች ከጋራዥ ተመላሽ የመኪና መለዋወጫዎች እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Cooperative-Bank-of-Oromia-S.C-Log-4

Overview

 • Category : Office Items & Equipment sale
 • Posted Date : 05/21/2021
 • Phone Number : 0115576174
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/07/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ያገለገሉ የቢሮ ወንበር እና ጠረጴዛዎች፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፣  ንቃይ የአሉሚኒየም ፓርትሽኖች፣ የአሉሚኒየም እና የብረት በሮች፣ አሮጌ ጎማዎች፣ የመኪና ባትሪዎች ፣ ከጋራዥ ተመላሽ የመኪና መለዋወጫዎች እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

 1. የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) ያላችሁ ተጫራቾች ቦሌ መንገድ ጌት ሃውስ ህንፃ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ላገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 100 (አንድ መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን  በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ደምበል ሲቲ ሴንተር  አንደር ግራውንድ  በሚገኘው  BMS 01B ቢሮ ቁጥር  ወይም   የባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ፤
 2. የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ጦር ሃይሎች ከሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ጀርባ ጋና ኤንባሲ ከመድረሶ በፊት በስተ ግራ በሚያስገባው ኮብል ስቶን  መንገድ  ከኦሜጋ አፀደ ህፃናት ት/ቤት 100 ሜትር ተሸግሮ  በሚገኘው የባንኩ ግምጃ ቤት  በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሁም ግንቦት 26 እና 30 ቀን  2013 ዓ.ም  ከጧቱ 4፡00 ሰዓት እከከ 10፡00 ሠዓት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
 3. ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ቦሌ መንገድ ደምበል ህንጻ BMS 01B ቢሮ ቁጥር ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ፡፡
 4. የሚጫረቱበትን ንብረት የጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶዉን) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% በተጨማሪነት መኖር አለመኖሩን በግልፅ በሰነዱ ላይ በፅሁፍ መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
 7. አሸናፊ መሆናቸው የተገለፀላቸው ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያውን በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ጠቅላላ የሲፖኦ ዋጋ ውርስ ይደረጋል፡፡
 8. ጨረታው ሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በ10፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ማክሰኞ  1 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ደምበል ሲቲ ሴንተር በ6ኛው አሳንሰር 4ኛ ፎቅ  ግዥ እና ፋሲሊቲ አስተዳደር ወይም 9ኛ ፎቅ ምክትል ፕሬዘዳንት ፋይናንስ ና ፋሲሊቲዎች ቢሮ ፣ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተጫራቾች ባልተገኙበት የጨረታ ሰነዱ  የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 9. ባንኩ የተሸለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)

ስልክ ቁጥር 0115576174

.ሣ.ቁ 16936

Send me an email when this category has been updated