የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በወሊሶ ከተማ ያስገነባዉን ባለ ሦስት ፎቅ ሕንፃ ውስጥ የተለያዩ ስፋት ያላቸዉን ክፍሎችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Cooperative-Bank-of-Oromia-S.C-Log-2

Overview

 • Category : House & Building Rent
 • Posted Date : 06/11/2021
 • Phone Number : 0113411748
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/26/2021

Description

የኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በወሊሶ ከተማ ያስገነባዉን ባለ ሦስት ፎቅ ሕንፃ ውስጥ ( ለሱፐር ማርኬት’ ለቢሮ ‘ ለካፌና ሬስቶራንት ‘ ለጂምናዚየም ‘ለውበት ሳሎን ‘ለወንዶች ፀጉር ቤት’ለማሳጅ ‘ሳውና እና ስቲም ‘ለስብሰባ አዳራሽ እና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚዉሉ) የተለያዩ ስፋት ያላቸዉን ክፍሎችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት በኪራይ ጨረታዉ ላይ መሳተፍ  የሚፈልግ ማንኛዉም ተጫራች ቀጥሎ በተዘረዘሩት መመሪያ መሠረት አስፈላጊዉን መስፈርቶች በማሟላት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 1. ተጫራቾች ከንግድ ዘርፉ ጋር ተያያዥ የሆኑትን የንግድ ምዝገባ፤የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የንግድ ስያሜ የማስታወቂያ ምልክት ፈቃድ ኮፒ በማያያዝ ወይም ለወደፊት ማቅረብ እንደሚችሉ መጥቀስ ይኖርባቸዋል፤
 2. ተጫራቾች ለጨረታ ከቀረቡት የካሬ ሜትር መጠን በተጨማሪ ሊያዉቁት የሚገባቸዉ በጋራ ለሚጠቀሟቸዉ እንደ መፀዳጃ ቤትና መተላለፊያ ኮሪደሮች የፅዳትና የጥገና ክፍያዎችን የመብራት፤ ዉሃ፤ ጀነሬተር  እና ሌሎች ተመሳሳይ  የጥገና ክፍያዎችን በጋራ እንደሚከፍሉ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፤
 3. የአንድ ካሬ ሜትር እና የጠቅላላ ካሬ ሜትር የሚከራዩበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር እና የአከፋፈል ሁኔታን በትክክል መጥቀስ ይኖርባቸዋል፤
 4. የሚከራዩትን የሕንፃዉን ክፍሎች በወሊሶ ከተማ በሚገኙት የባንካችን የወሊሶ እና አይቱ ቅርንጫፎች አማካኝነት ተጫራቾች በስፍራዉ ተገኝተዉ በማየት አስፈላጊዉን መረጃዎች ማግኘት ይችላሉ፤
 5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ እስከ ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ወሊሶ እና  አይቱ ቅርንጫፎች ወይም ቦሌ መንገድ ደምበል ህንጻ ምድር ቤት ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል  በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የኪራይ ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት  ይችላሉ፤
 6. ጨረታው ሰኔ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ደምበል ሲቲ ሴንተር በ6ኛው አሳንሰር 4ኛ ፎቅ  ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡
 7. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
 8. ለጨረታ የቀረቡት ክፍሎች አገልግሎት ዓይነትና ስፋት ዝርዝር ከባንኩ ንብረት አስትዳደር ‘ወሊሶ እና አይቱ ቅርንጫፎች ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ ወሊሶ ቅርንጫፍ ስልክ ቁ 0113411748/81 ፤ አይቱ ቅርንጫፍ ስልክ ቁ 0113664885 እና የባንኩ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር BMS-01B ስልክ ቁ. 0115576174 በመደወል በቂ መረጃ ማግኘት ይችላሉ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)

ለላቀ ለውጥ የቆመ !

Send me an email when this category has been updated