የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አክስዮን ማህበር በተሻሻለ አዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለብድሩ መከፈል ዋስትና/መያዣ እንዲሆን ሥልጣን በወ/ሮ ሕይወት ተረፈ አስፋዉ ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን ንብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Cooperative-Bank-of-Oromia-S.C-Log-2

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 07/30/2022
 • Phone Number : 0911877319
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/03/2022

Description

 የኦሮሚያ ኀብረት ሥራ ባንክ

   ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አክስዮን ማህበር አዳማ ቅ/ፍ ኦብሲዲያ ኢንዱስትሪያል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ላበደረዉ ብድር ብድሩ በዉሉ መሰረት ስላልተከፈለ ባንኩ በተሻሻለ አዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለብድሩ መከፈል ዋስትና/መያዣ እንዲሆን ሥልጣን ባለው የመንግስት አካል የተመዘገበውንና በወ/ሮ ሕይወት ተረፈ አስፋዉ ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን ንብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ብድር ዕዳዉ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች ሐራጁ በሚካሄድበት ዕለት ንብረቱ በሚገኙበት አድራሻ በመቅረብ በጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ተጋብዟል፡፡

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም የንብረት ዓይነት አበዳሪዉ ቅርንጫፍ ለጨረታ የቀረበው ንብረት አድራሻ የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር የጨረታ መነሻ  ዋጋ ብር ጨረታው የሚካሄድበት ቀን፣ ቦታ እና ሰዓት

ዞን

 

ክ     ወረዳ ቀበሌ የቤት ቁጥር የካርታ ቁጥር
1 ኦብሲዲያ ኢንዱስትሪያል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር  

ወ/ሮ ሕይወት ተረፈ አስፋዉ

 

የመኖሪያ ቤት

አዳማ  

ምስ/ሸዋ

 

አዳማ

 

በሬቻ

 

 

73232/97

 

205 ካ.ሜ

  7,352,097.33 ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት ከ 4፡00- 6፡00 ንብረቱ በሚገኝበት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ጨረታዉን እናካሂዳለን፡፡

ተጫራቾች እንዲያውቋቸው

 1. ተጫራቾች ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼(25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ስም አሰርተው ይዘው በመቅረብ ቅርንጫፉ በሚገኝበት አድራሻ ቀርበው በመመዝገብ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡ ጨረታውን በድርጅት ስም የሚጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገበ፣ ንግድ ፍቃድና የድርጅቱን ውክልና ማቅረብ አለበት::
 2. ጨረታው ከላይ ቀንና ሰዓቱ በተገለፀው መሠረት ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለጨረታ የቀረበው ንብረት ባለበት ጊቢ ውስጥ ይካሄዳል! ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
 3. ንብረቱን በሥራ ሰዓት መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በስልክ ቁጥር 09-11–87-73-19/022-111-78-66 በመደወል መጠየቅና መጎብኛት ይቻላል፡፡
 4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አሥራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
 5. የጨረታው አሸናፊ በሀገሪቱ ህግ መሠረት ለመንግስት የሚከፈለውን ማንኛውንም የታክስ ክፍያ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን ከፍሎ ስሙን ወደ ራሱ የሚያዛዉር ይሆናል፡፡
 6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ