የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከአገልግሎት ዉጭ የሆኑ እና ታትመዉ ሥራ ላይ ያልዋሉ የህትመት ሰነዶች ፤ የማስታወቂያ ወረቀቶች እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡

Cooperative-Bank-of-Oromia-S.C-Log-1

Overview

  • Category : Other Sale
  • Phone Number : 0115576082
  • Source : Reporter
  • Posted Date : 05/15/2022
  • Closing Date : 05/26/2022

Description

Baankii Hojii  GamtaaOromiyaa

  የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከአገልግሎት ዉጭ የሆኑ እና ታትመዉ ሥራ ላይ ያልዋሉ የህትመት ሰነዶች ፤ የተለያዩ የፕሪንተር እና የፋክስ ቀለሞች ፤ የተለያዩ ዩኒፎረም ጨርቆች ፤ አዲስ የሊፋን ሞተር ብርጅስቶን ጎማዎች ፤ የሴት ጫማዎች ፤የተለያዩ ያገለገሉ የማስታወቂያ ባነሮች ፤  የማስታወቂያ ወረቀቶች  እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-

  1. የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 18 ቀን 2014 ድረስ ባሉት 10 የስራ ቀናት ዉስጥ ቦሌ መንገድ ጌት ሃውስ ህንፃ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ ላገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200 (ሁለት መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB 1446500010001 በማስገባትና ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ደንበል ሲቲ ሴንተር ምድር ቤት ንስር ማይክሮ ፋይናንስ ዋናው መ/ቤት አጠገብ የባንኩ ግምጃ ቤት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ደንበል ሲቲ ሴንተር ምድር ቤት በሚገኘው የባንኩ ግምጃ ቤት በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በኋላ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ ቀጥሎ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ከግንቦት 14 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  3. ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ቦሌ ደንበል ሲቲ ሴንተር ምድር ቤት ንስር ማይክሮ ፋይናንስ ዋናው መ/ቤት አጠገብ የባንኩ ግምጃ ቤት አስተዳደር ዋና ክፍል ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. የሚጫረቱበትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO ) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% በተጨማሪነት መኖር አለመኖሩን በግልጽ በሰነዱ ላይ በጽሁፍ መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ጨረታው ሀሙስ ግንቦት 18 ቀን 2014ዓ.ም. ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ተዘግቶ አርብ ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠዋት 3፡00 ሰዓት ራንግ ሪል ስቴት ህንፃ 7ኛ ፎቅ የባንኩ ግዥና አቅርቦት ዋና ክፍል ቢሮ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ተጫራቾች ባልተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)

ስልክ ቁጥር 0115576082

ፖ.ሣ.ቁ. 16936