የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች ፤ ኮምፒውተሮች ፤ ፕሪንተሮች ፤ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፤ የባንክ ካውንተር እና ኬጂዎች እምነ በረዱን ጨምሮ፤ አሉሚኒየም ፓርቲሽኖች ፤ የጥበቃ ቤቶች ፤ እና የተለያየ መጠን ያላቸው ወንበርና ጠረጴዛዎች የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡
Overview
- Category : Other Sale
- Posted Date : 12/24/2022
- Phone Number : 0115576174
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/07/2023
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች ፤ ኮምፒውተሮች ፤ ፕሪንተሮች ፤ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፤ የባንክ ካውንተር እና ኬጂዎች እምነ በረዱን ጨምሮ፤ አሉሚኒየም ፓርቲሽኖች ፤ የጥበቃ ቤቶች ፤ እና የተለያየ መጠን ያላቸው ወንበርና ጠረጴዛዎች የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፤00 ሰዓት ድረስ ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ ላገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 100 ( ብር አንድ መቶ ) በሂሳብ ቁጥር ETB 1446500010001 በማስገባትና ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ሩዋንዳ ባንኩ እያስገነባ ባለው ህንፃ አጠገብ ባለው ራንግ ሪል ስቴት ህንፃ 7ኛ ፎቅ የባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ቻይና ጋራዥ ተብሎ በሚጠራው ትይዩ ሱሉልታ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን መ/ቤት በኩል ወደ ውስጥ በሚያስገባው ጥርጊያ መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የባንኩ ዕቃ ማከማቻ መጋዘን በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ፤ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሁም ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፤00 ሰዓት እስከ 10፤00 ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፤00 ሰዓት ድረስ ቦሌ ሩዋንዳ ራንግ ሪል ስቴት ህንፃ 7ኛ ፎቅ የባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የሚጫረቱበትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO ) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT ) 15% በተጨማሪነት መኖር አለመኖሩን በግልጽ በሰነዱ ላይ በጽሁፍ መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው አርብ ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 6፤00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት ከቀኑ 7፤00 ሰዓት ራንግ ሪል ስቴት ህንፃ 7ኛ ፎቅ የባንኩ ፋሲሊቲና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)
ስልክ ቁጥር 0115576174
ፖ.ሣ.ቁ. 16936
———————- ለላቀ ለውጥ የቆመ ! ————————–