የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማኅበር በተለያዩ የክፍል ደረጃ የተማሪ መማሪያ መጽሐፍቶች እና የመምህሩን መምሪያ መጽሐፍት አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Printing & Publishing Service
 • Posted Date : 08/24/2022
 • Phone Number : 0118962008
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/03/2022

Description

  የጨረታ ማስታወቂያ 002/2014

የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማኅበር በተለያዩ የክፍል ደረጃ የተማሪ መማሪያ መጽሐፍቶች እና የመምህሩን መምሪያ መጽሐፍት አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡

የስራው ዓይነት፡- ሕትመት

ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

 1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣በግዢ ኤጄንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀን ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን  ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የመጨረሻ ጨረታው የሚዘጋው ማስታወቂያዉ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በ 10ኛዉ ቀን  በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት  በማግስቱ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ቢድ ቦንድ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ፐርሰንት) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ ቼክ) ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል መወዳደር ይቻላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ከማህበሩ ባገኙት የፋይናንስ ሰነድ ላይ ሳይለወጥ በመስራት በስም በታሸጉ ኢንቨሎፕ የጨረታውን የማስታወቂያ ቁጥር በመጥቀስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 6. ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
 7. የጨረታ ማወዳደሪያ ዋጋ የሚሞላው ማኅበሩ ባቀረበው ቅጽ ላይ ሳይለወጥ በእስክርቢቶ መሆን አለበት፡፡ ቅጹ ከተለወጠ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 8. በጨረታ የቀረበዉ የሚታተመዉ መፀሀፍ ብዛት ቁጥር    979,698  (ዘጠኝ መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺ ስድስት መቶ ዘጠና ስምንት )  ሲሆን  ተጫራቾች   የመፀኀፍ  ብዛት  በ 50%  እና በ 100%  ዋጋ  ሞልተዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
 9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሰነድ መግዣ የማይመለስ 00 (ሁለት መቶ ብር )ከፍለዉ መዉሰድ ይችላሉ፡፡

ማስታወሻ፡- 10ኛው ቀን እለቱ እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዛወራል፡፡

አድራሻ፡–  ቡልጋሪያ ኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪ  በስተግራ ሲታጠፉ የቀድሞ  ሰላም ክሊኒክ አጠገብ እንገኛለን ፡፡ ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር  ( 0118 96 20 08 ወይም È0905050887

WALDAA MANNEEN BARNOOTA DHUUNFAA OROMIYAA

                     የኦሮሚያ  የግል  ት/ቤቶች  ማህበር

   OROMIA PRIVATE SCHOOLS ASSOCIATION

                   0118 962008        0905050887       Addis Abeba