የከሠረው ጌት ላይን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኃ.የተ.የግል.ማህበር ሰንሻይን ኮንስትራክሽን መጋዘን ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-65433 ኢት ሲኖ ትራክ ገልባጭ መኪና ባለበት ሁኔታ በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Vehicle Foreclosure
  • Posted Date : 10/15/2022
  • Phone Number : 0921146680
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/04/2022

Description

የከሠረው ጌት ላይን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኃ.የተ.የግል.ማህበር 

በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የከሠረው ጌት ላይን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ንግድ ችሎት የመክሠር ፍርድ ሰጥቷል ፡፡ስለሆነም ማህበሩ ያለበትን ዕዳ መክፈል እንዲችል ከታች በሠንጠረዥ ውስጥ የተገለጸውን አዲስ አበባ አቃቂ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን መጋዘን ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-65433 ኢት ሲኖ ትራክ ገልባጭ መኪና ባለበት ሁኔታ በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የሞተር ቁጥር የሻንሲ ቁጥር የተመረተበት ጊዜ የሰሌዳ ቁጥር የሐራጅ መነሻ
1 መኪናው ሲንቀሳቀስ የሚነበብ ነው፤ LZZ5END27D772944    እ.ኤ.አ ጥቅምት 2013 ኢት 3-65433 1,500.000.00

ማሳሰቢያ

1.ለሐራጅ የተመዘገቡ ተጫራቾች በራሳቸው ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው አማካይነት ሐራጁን መሳተፍ ይችላሉ፡፡

2.ለሐራጅ የቀረበውን ከላይ በሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰውን መኪና አቃቂ ሰንሻን ኮንስትራክሽን መጋዘን ግቢ ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡

3.ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የሐራጅ መነሻ ዋጋ 1/10 (አንድ አስረኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) በከሠረው ጌት ላይን ኢንትርናሽናል ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ስም  በማሰራት የጨረታው ማስታወያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም  ባሉት ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ10፡00 ሰዓት ድረስ ልደታ ፍሊንትስቶን ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቁጥር 259 በሚገኘው ቢሮ መመዝገብ አለባቸው፡፡

4.የመኪናው የሐራጅ ሽያጭ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም  ልደታ ፍሊንትስቶን ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቁጥር 259 በሚገኘው ቢሮ   ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በዕለቱ ይሸጣል፡፡
5.የሐራጅ አሸናፊዎች የሚፈለገውን ክፍያ ከፈፀሙ በኃላ መኪናውን በ10 ቀናት ውስጥ ከቦታው ላይ ማንሳት አለባቸው፡፡

6.ማንኛውም የስም ማዛወሪያ ፣ያልተከፈለ የጉምሩክ ቀረጥ፣ቫት እና ሌሎች ተዛማጅ ክፍያዎች የሐራጅ አሸናፊ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡

7.የመኪናው የባለቤትነት ስም እንዲዛወር መርማሪ ዳኛው ወይም ንብረት ጠባቂው ለሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ደብዳቤ ይጽፋል፡፡

8.ሻጭ ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  1. ተጫራቾች መኪናው በሚገኝበት ቃሊቲ ሸዋ ዳቦ ጀርባ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ግቢ ውስጥ የሚገኝ ስለሆነ በስልክ ቁጥር 0910 71 04 95 በማናገር መኪናውን በአካል ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 21 14 66 80፣0911 125677፣0928 821709፣ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፣

የከሠረው ጌት ላይን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ ማህበር ጽ/ቤት