የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት በራሱ ህንፃ ውስጥ የሚገኘውን ለፎቶ ኮፒና የመጠረዝ ሥራ አገልግሎት የሚውል አንድ ክፍል ለማከራየትና አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡

CCRDA-Logo-Reporter-Tenders-2

Overview

  • Category : House & Building Rent
  • Posted Date : 06/11/2021
  • Phone Number : 0114390322
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/24/2021

Description

በድጋሚ የወጣ የፎቶ ኮፒና የመጠረዝ ሥራ ቤት ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት CCRDA ከ400 በላይ አባላት ያሉትና ከ46 ዓመታት በላይ በልማትና በጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡

ድርጅቱ በራሱ ህንፃ ውስጥ የሚገኘውን ለፎቶ ኮፒና የመጠረዝ ሥራ አገልግሎት የሚውል አንድ ክፍል ለማከራየትና አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም በሞያው ልምድ ያለውና በራሱ መሳሪዎች ለድርጅቱ አገልግሎት መስጠት የሚችል መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪ ተከራዩ ለሌሎች የውጪ ተገልጋዮች አገልግሎት መስጠት ይችላል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ለኪራይ የቀረበውን ክፍል ካዩ በኋላ የሚከተሉትን ማቅረብ አለባቸው፡-  

  1. በተለያዩ የወረቀት መጠኖች የኮፒ # የመጠረዝና የላምኔቲንግ ሥራ የሚሠሩበትን የዋጋ ዝርዝር
  2. ከዚህ ቀደም በሞያው ያላቸውን የሥራ ልምድ የሚያሳይ ማስረጃ
  3. የግብር ከፋይ (Tin No) ቅጂ
  4. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ቅጂ
  5. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር) በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል

ተጫራቾች ለመከራየት የሚያቀርቡትን ዋጋ ከላይ በዝርዝር ከተጠቀሱት ማስረጃዎች ጋር በማያያዝ በክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት መ/ቤት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውሰጥ ቢሮ ቁጥር 304 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

                  የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት

     አድራሻ፡- ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎችና ሜካኒኮች ማሰልጠኛ ማዕከል ፊት ለፊት

                ስልክ 0114-390322 ወይም 0114-393393

Send me an email when this category has been updated