የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) አገር በቀል የበጎ አድራጎት ማህበር የማርቼዲስ ፣ የዳፍ እና የሌይላንድ ከባድ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

CCRDA-Logo-Reporter-Tenders

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 07/02/2021
  • Phone Number : 0114390322
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 07/15/2021

Description

በድጋሚ የወጣ የከባድ ተሽከርካሪዎችና ተሳቢዎች መለዋወጫዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ    

ጨረታ ቁጥር 001/2013

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) አገር በቀል የበጎ አድራጎት ማህበር የማርቼዲስ ፣ የዳፍ እና የሌይላንድ ከባድ ተሽከርካሪዎች እና የባወር ፣ ኑትቡም ፣ ካላብሬዝ ፣ ጆስት እና የሌሎች ተሳቢዎች በተጨማሪ የክሬኖች እና ፎርክሊፍት መለዋወጫዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች፡-

1.ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽና የምድብ ዝርዘር ለእያንዳንዱ የምድብ ዓይነት ወይም ለጠቅላላው የማይመለስ ብር 150/አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ እየከፈሉ አዲስ አበባ ከተማ ቃሊቲ የመንገድ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎችና ሜካኒኮች ማሰልጠኛ ፊትለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡

2.ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከኦሪጂናሉ የመጫረቻ ሰነድ ጋር እባሪ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ አሸናፊ ለሆኑት የጨረታ ማስከበሪያው በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ የሚታሰብ ይሆናል፡፡ ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

3.ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉትን መለዋወጫ በሙሉ ዋጋ በ10 ቀናት ከፍለው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡

4.ተጫራቾች ስለ ንብረት አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

5.ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114 39 33 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

6.ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

           የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA)

አድራሻ፤ ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎችና ሜካኒኮች ማሰልጠኛ ማዕከል ፊት ለፊት

ስልክ 0114-390322 ወይም 0114-393393

Send me an email when this category has been updated