የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት ስራዎችም በትክክል መተግበራቸውን ለማወቅና በመረጃ የተደገፈ ለማድረግ የሚረዳ የመለያ ካርድ የመጠየቀም ስርዓትን ለመተግበር አቅዷል፡፡

CCRDA-Logo-Reporter-Tenders

Overview

 • Category : Software purch. & Dev. Service
 • Posted Date : 01/04/2023
 • Phone Number : 0911643937
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/16/2023

Description

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት

Consortium of Christian Relief and Development Association (CCRDA)

የጨረታ ማስታወቂያ

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (ክ.በ.አ.ል.ማ.ህ)/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ኘሮጀክት ፖሊዮን ከሀገራችን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ  እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህም ጋር በተገናኘ በአሁኑ ወቅት የህብረተሰብ አቀፍ በሽታዎችን አሰሳና ቅኝት በመመስረትና በማስፋፋት በኢትዮጵያ በ 88 አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር ወረዳዎች ላይ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የህብረተሰብ አቀፍ በሽታዎች አሰሳና ቅኝት የሚተገበረው ከህብረተሰቡ በተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው ከ 4500 በላይ የሚሆኑ በጎ ፈቃደኞች ከላይ በተገለፁ ወረዳዎች ውስጥ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ በጎ ፈቃደኞች ነፍሰ ጡር እናቶችን መለየት እና ለቅድመ ወሊድ እንክብካቤ ወደ ጤና ተቋማት ማስተላለፍን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ተግባራትን ያከናውናሉ፣ ለምሳሌ ምንም ክትባት ያላገኙ ህጻናትን፣ አዲስ የተወለዱ ሕፃናትን መለየትና የክትባት ክትትል ማድረግ፣ ክትባት ያቋረጡ ህጻናትን መለየት፣ ነፍሰጡር እናቶችን መለየት እና በአቅራቢያው ላለው የጤና ተቋም ማሳወቅ ይገኙበታል። እነዚህ ስራዎችም በትክክል  መተግበራቸውን ለማወቅና በመረጃ የተደገፈ ለማድረግ የሚረዳ የመለያ ካርድ የመጠየቀም ስርዓትን ለመተግበር አቅዷል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የምታሟሉና በመስኩ የተሰማራችሁ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

 • ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ኮፒና የግብር ከፋይ መታወቂያ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር መመሪያ (ToR)፣ የሚፈለገውን የካርድ አይነት ናሙና እና የሚታተሙት አርማዎችን እንዲሁም ቁልፍ የጽሁፍ መልእክቶችን፣የካርዱ ስፋት፣ ቁመት፣ የሚታተምበት ወረቀት ጥራትና እይነት፣ የላሚኔሽን/ጥረዛ፣ የህትመት ቀለም አይነት እና የካርድ ብዛት እንዲሁም አሰራር ከዚህ በታች በተመለከተው አድራሻ በሥራ ሰዓት ቀርበው  መውሰድ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከሚሰጡት ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ ወይም በጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ለስራው የሚጠይቁትን የገንዘብ ዋጋ እና የህትመት ውጤቶቹን አጠናቀው የሚያስረክቡበትን ጊዜ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች ከዚህ በፊት በድርጅታቸው የተሰራ የማይመለስ ተመሳሳይ ሥራ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በሚያቀርቡት ናሙና ላይ የድርጅታቸው ህጋዊ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
 • ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የሪፈራል ካርድ ጨረታ ብለው በተናጥል መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 8 ቀን 2015ዓ.ም. በክ.በ.አ.ል.ማ.ህ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ በ8 ሰዓት ይከፈታል፡፡
 • ክ.በ.አ.ል.ማ.ህ/ኮር ግሩኘ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ለበለጠ መረጃ – 0911643937/0911427891

አድራሻ:          

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደብረዘይት መንገድ

ቃሊቲ መንገድ ትራንስፖርት ፊት ለፊት

ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304