የዊማ ኢንተርናሽናል ኢንክ ዋና ቢሮ ያገለገሉ ቶዮታ ላንድ ክሩውዘር ስቴሽዋገን 2003 ሞዴል እና ኪያ ሪዮ አውቶሞቢል 2017 ሞዴል መኪናዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

WEEMA-logo

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 11/16/2022
  • Phone Number : 0118688651
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/06/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

 የዊማ ኢንተርናሽናል ኢንክ ዋና ቢሮ ያገለገሉ ቶዮታ ላንድ ክሩውዘር ስቴሽዋገን 2003 ሞዴል እና ኪያ ሪዮ አውቶሞቢል 2017 ሞዴል  መኪናዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረው ላይ መወዳደር ይችላል፡፡

የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት፡- ተጫራቾች የተሸከርካሪ የጨረታ ሠነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ቢሮ መውሰድ ይቻላል፡፡

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለጨረታ የተዘጋጁትን ተሽከርካሪዎቹ በሚገኙበት አድራሻ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁጥር 548 ዊማ ኢንተርናሽናል ኢንክ ቢሮ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፤
  2. ተጫራቾች ሊገዙት ለሚፈልጉት መኪና የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ሰነድ ውስጥ በተዘጋጀው የተሸከርካሪ ዋጋ ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ በድርጅቱ ዊማ ኢንተርናሽናል ኢንክ  ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በአስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ  ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በአስራ አምስተኛው ቀን ግን ሰነዱ የሚገባው እስከ አራት ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡

3.ተጫራቾች ለሚጫረቱበት መኪና ጨረታ ማስገቢያ /ቢድቦንድ/ የሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ በዊማ ኢንተርናሽናል ኢንክ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /ሲፐኦ/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ፖስታ ሲሰጡ አብሮ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ጨረታው 27/03/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን አሸናፊው ወዲያው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ 5 (አምስት ) ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ በጨረታው አሸንፈው ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊዎች መኪናውን የማጓጓዣ ወጭዎችን፡ ስም ማዞሪያና ሌሎች ተያያዥ ወጭዎችን ይሸፍናሉ፡፡
  2. በጨረታው ለሚሸነፉት ያስያዙትን የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የጨረታው አሸናፊ ሙሉ ክፍያውን እንደፈጸመ የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡

6.ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

    አድራሻ፡- አዲስ አበባ  መገናኛ ቦሌ ክ/ከተማ  የጀርባ በር  ወደ እግዛቤር አብ ቤ/ክ  በሚወስደው መንገድ  500  ሜትር  ገባ ብሎ  ከላይን ሴኩሪቲ  ቢሮ  ፊት  ለፊት

አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁጥር 548

                 የመስመር ስልክ ቁጥር  +251118688651

                       የሞባይል ስልክ ቁጥር  +251911566701