የዓባይ ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች አስራ ሦስተኛ መደበኛ እና ሰባተኛ አስቸኳይ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የጥሪ ማስታወቂያ፤

Announcement
abay-bank-logo-3

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 10/26/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/19/2022

Description

የዓባይ ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች አስራ ሦስተኛ መደበኛ እና ሰባተኛ አስቸኳይ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የጥሪ ማስታወቂያ፤

የዓባይ ባንክ አ.ማ የባለአክስዮኖች አስራ ሦስተኛ መደበኛ እና ሰባተኛው አስቸኳይ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሕዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የባንኩ ባለአክስዮኖች በተጠቀሰው ቀንና ቦታ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

 1. የአስራ ሦስተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፤
  • ድምጽ ቆጣሪዎች መሰየምና ማጽደቅ፣
  • ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
  • የጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ፣
  • የአዳዲስ አክሲዮኖች ሽያጭ እና የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ፣
  • የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣
  • የውጭ ኦዲተሮች ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣
  • ከላይ በተራ ቁጥር 1.5 እና 1.6 በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
  • የዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
  • የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አበልና የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፣
  • የውጭ ኦዲተር ሹመት ማጽደቅና ክፍያ መወሰን፣
  • የቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ፡
  • የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ
 2. የሰባተኛው አስቸኳይ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፤
  • ድምጽ ቆጣሪዎች መሰየምና ማጽደቅ፣
  • ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
  • የጉባኤውን ረቂቅ አጀንዳ ማጽደቅ፣
  • የባንኩን ካፒታል ለማስደግ ተወያይቶ መወሰን፤
  • የባንኩን መመሥረቻና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል፤
  • የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ

ባለአክስዮኖች የታደሰ መታወቂያ ካርድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ በግንባር በመገኘት ወይም የባለአክስዮኖች ህጋዊ ተወካዮች አግባብነት ካለው የመንግስት አካል የተሠጠ ውክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የወካይና ተወካይ የመታወቂያ ካርድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ይዛችሁ በጉባኤው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ በጉባኤው ላይ በግንባር መገኘት የማትችሉ ባለአክስዮኖች ከስብሰባው ዕለት ሶስት ቀን ቀደም ብሎ ባንኩ ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በመሙላት ተወካዮቻችሁን ማሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ በተጨማሪም ጆሞ ኬንያታ መንገድ፣ ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንጻ በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0115549735 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዓባይ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ