የዕድገት በሕብረት የገበያ አዳራሽ አክሲዮን ማህበር የግቢ ማስተካከል ሥራ ፣ የአሉሚኒየም ሥራ እና የኤሌክትሪክ ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Electronics Equipment
- Posted Date : 12/24/2022
- Phone Number : 0113489092
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/04/2023
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የዕድገት በሕብረት የገበያ አዳራሽ አክሲዮን ማህበር
የግቢ ማስተካከል ሥራ ፣ የአሉሚኒየም ሥራ እና የኤሌክትሪክ ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ደረጃ 5 ወይም ከዚያ በላይ ሆኖ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸውን ተቋራጮች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው /ያላት
- Company Profile ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው /ያላት ፤
- ተጫራቾች የተ.እ.ታ ( VAT) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በዚህ ጨረታ ለመወዳደር ለሚፈልጉ ተጫራቾች የሥራውን ዝርዝር (Specification) የጨረታ ሰነዱን ከአ/ማህበሩ ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ከዚህ ቀደም ሲሰሩ ከነበረ መንግስታዊና የግል ድርጅቶች የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ ቀናት ከድርጅቱ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በየአንዳንዱ በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታውን ዋጋ 2% ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ ጋር በባንክ በተመሰከረ ትክክለኛ ሲፒኦ (C.P.O) ወይም ባንክ ጋራንቲ ለእያንዳንዱ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታውን 10% ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ ጋር በባንክ በተመሰከረ ትክክለኛ ሲፒኦ (C.P.O) ወይም ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሥራውን የሚያጠናቅቁበትን ጊዜ ለእያንዳንዱ በተናጥል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ካለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውንና የሚጫረቱበትን የጨረታ አይነት በመለየትና በመፃፍ በመስራቤቱ ጽ/ቤት በተዘጋቸው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 (ሰባት) ቀናት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ሰኞ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ./ም ከቀኑ 9፡30 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- አ/ማህበሩ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113 48 90 92 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ዕድገት በሕብረት የገበያ አዳራሽ አክስዮን ማህበር
(ዘነበወርቅ የቀለበት መንገድ ድልድይ አጠገብ)