የጀርመን ትብብር ድርጅት ኢንቬስት ፎር አፍሪካ ለስራ ዕድል ፈጠራና ሰልጠና የቀረበ ልዩ ፕሮግራም፡- ፍላጎቱ ላላቸው የቀረበ ጥሪ

Giz-office-Logo

Overview

  • Category : Announcement
  • Posted Date : 12/19/2022
  • Phone Number : 0913564425
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/18/2023

Description

የጀርመን ትብብር ድርጅት

ኢንቬስት ፎር አፍሪካ

ለስራ ዕድል ፈጠራና ሰልጠና የቀረበ ልዩ ፕሮግራም፡- ፍላጎቱ ላላቸው የቀረበ ጥሪ

“ኢንቬስትመንት ፎር ጆብስ” በሚል መርህ በመመራት የጀርመን ፌዴራል የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር (ቢኤምዜድ) ለስራ ፈጠራ እና ስልጠና የቀረበ ልዩ ፕሮግራም ሲሆን በተመረጡ አካባቢዎች እና የኢኮኖሚ ሴክተሮች (ክላስተሮች) ኢንቬስት ፎር ጆብስ በሚል መርህ በተመረጡ የአፍሪካ ሃገሮች ኢኮኖሚ ውስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ በጀርመናውያን፣ በአውሮፓውያን እና በአፍሪካውያን ኢንቬስተሮች የስራ አድል የመፍጠር ፕሮግራም በሚል መመሪያ የሃገራቱ ዜጎች የኢኮኖሚ ሁኔታን ማሻሻል ይፈልጋል፡፡ የኢንቬስት ፎር ጆብስ ዋና አላማ ብዙ እና የተሻሉ የስራ እድሎችን መፍጠር ነው፡፡ በተጨማሪም የግል አልሚ ባለሃብቶች ኢንቬስትመንት ስራ እንዲጨምር እና ዘላቂ እንዲሆን የፕሮግራሙ አላማ ነው፡፡

ፕሮግራሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነታቸውን እና ምርታማነታቸውን በማሳደግ ኢንተርፕራይዞቹ የሚያመርቷቸው ምርቶች እና የሚሰጧቸው አገልግሎቶች የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ገበያ ፍላጎትን እንዲያሟሉ አላማ የሰነቀ ፕሮግራም ነው፡፡ ፕሮግራሙ በሴቶች ለሚተዳደሩ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልዩ ትኩረት የሚሰጥ ሲሆን ለሴቶች ስራ እድል ፈጠራ እና ለስራ ቅጥር ብቁ የሚያደርጋቸው ስልጠና ለመስጠት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡

በፕሮግራሙ ተጠቃሚ የሚሆኑ ድርጅቶች የማምረቻና መገልገያ ቁሳቁሶች፣ የአስተዳደር ማማከር ስልጠና፣ የቴክኒክ ስልጠና፣ የፋይናንስ ብቃት/ የንግድ ስራ እቅድ ልማት፣ ተግባራዊ የጥናት ስራዎች፣ ወ.ዘ.ተ ድጋፍ የሚቀርብላቸው ይሆናል፡፡ ፕሮግራሙ ድርጅቶቹ የፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽነት እንዲኖራቸው ልዩ የማማከር አገልግሎት ድጋፍ የተለየ ትኩረት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ የፋይናንስ ድጋፉ እቅድ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞቹ የአስተዳደር መሻሻል እና የንግድ ስራ እድገት እንደሚያመጣ ይጠበቃል፡፡ ፕሮጀክቱ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞ ች በሶስት ምድቦች ድጋፍ ለማድረግ አቅዷል፡፡

  1. የሚቀርበው ድጋፍ :-“የስራ ተቀጣሪነት”

ፕሮጀክቱ ሙያ የሌላቸው ሰራተኞች በቅድመ-ቅጥር እና ስራ በሚሰሩ ጊዜ በሚሰጣቸው ስልጠና የተቀጣሪነት ተፈላጊነታቸው እንዲጨምር በማቀድ ለሁለት የተመረጡ መካከለኛ እና ከፍተኛ ድርጅቶች ሰራተኞቻቸውን በሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ አማካሪዎች ስልጠና እንዲያገኙ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ይህ ተግባር ድርጅቶቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ስራ እንዲሰሩ ወይም ኢንቬስት እንዲያደርጉ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

ኣጋር ኣካላት የካፒታል ወጪዎች ኢንቬስትመንት የሚያቋቁሙ ሲሆን አሁን ላይ ለሚሰሩት ስራ ተቀጣሪ ሰራተኞችን በመመልመል ከጂአይዜድ- ሴኳ ጋር ትብብር በማድረግ ለአዳዲስ ተቀጣሪ ሰራተኞች ስልጠና በመስጠት የሰራተኞቹን የመቀጠር ሁኔታ ማሻሻል ይፈልጋል፡፡

  1. የሚቀርበው ድጋፍ:- “ዲጂታል ገበያ መፍጠር”

ፕሮግራሙ ለተመረጡ አምስት የዲጂታል ገበያዎች እና የስራ እድል መፍጠሪያ ፕላትፎርሞች የንግድ ስራ ሞዴላቸው እንዲጠራ ለማድረግ፣ የቴክኖሎጂ ፕላትፎርሞች በማሻሻል ሁሉን አቀፍ እና አስተማማኝ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖራቸው፣ ለደንበኞች የሚያቀርቡት ምርት እና አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች እንዲቀርብ ለምሳሌ የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎች፣ የማስታወቂያ ስራዎች፣ በጽሁፍ መልዕክት እንዲገበያዩ፣ ከውጭ ምንጮች ተጨማሪ የኢንቬስትመንት ስራ እንዲሰሩ ድጋፍ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ፕሮግራሙ ለተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞች የባለሙያ ድጋፍ፣ የንግድ ስራ መስፈንጠሪያ ፕሮግራሞች፣ የመሳሪያ እና የገበያ እድል ድጋፍ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ በፕሮግራሙ ለአይቲ (IT) ባለሙያዎች፣ ለተለያዩ  ይዘት አዘጋጅ ባለሙያዎች፣ ለጥሪ አገልግሎት ሰራተኞች እና በዲጂታል ገበያ ስራው ጥሩ የስራ እድል እና የገቢ አማራጭ ለሚያገኙ ፍሊራንሰሮች የስራ እድል የሚፈጥር ይሆናል፡፡ ፕሮግራሙ የፍሊራንሰሮች የቅጥር ስርዓት መስፈርት ደረጃዎች ዝግጅት ድጋፍ የሚያቀርብ እና የቅጥር እድል እንዲሁም ግልፅ የሆነ የስራ ደሞዝ የአከፋፈል  ስርዓት እንዲተገበር ድጋፍ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

  1. የሚቀርበው ድጋፍ:- “የኢንስትመንት ዝግጁነት”

ፕሮግራሙ እስከ 25 ለሚደርሱ አምራች ኢንተርፕራይዞች እነዚህም የጨርቃ-ጨርቅ እና አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ወይም አገልግሎት ሰጪ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ በመስጠት ከፍተኛ እድገት እና የስራ ፈጠራ አቅም እንዲኖራቸው የሚያስችል ይሆናል፡፡ የተመረጡ ኢንተርፕራይዞች የሚወዳደሩ ሲሆን በዚህም የባለሙያዎች ቡድን የንግድ ስራ ሞዴላቸውን ይመዝናል እንዲሁም የንግድ ስራቸውን ማሳደግ እንዲችሉ ምክረ-ሃሳብ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ የተመረጡ ኢንተርፕራይዞች በግል ድጋፍ የሚቀርብላቸው ሲሆን ይህም በሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ አማካሪዎች ለድርጅቶቹ የሚቀርቡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እና የስራ  መሳሪያዎችን እንዲያገኙ የሚደረግ ይሆናል፡፡

አስፈላጊ ስልጠናዎች ማለትም ስትራቴጂካዊ የንግድ ስራ አስተዳደር፣ የፋይናንስ ሞዴል፣ የገበያ ልማት፣ ከኢንቬስተሮች ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት አስመልክቶ ስልጠና የመስጠት እና የማማከር ድጋፍ የሚቀርብላቸው ይሆናል፡፡ የሚቀርበው ድጋፍ ቁልፍ ውጤት ተብሎ የሚጠበቀው ቢያንስ 10 አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከውጭ የኢንቬስትመንት አጋሮች ስኬታማ የኢንቬስትመንት ድጋፍ እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡

አመልካቾች በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ፣ ከ2 ዓመት በላይ የቆዩ፣ በግል የሚተዳደሩ እና አስተማማኝ የፋይናንስ ደረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

በፕሮጀክቱ ለመሳተፍ ፍላጎቱ ያላችሁ አመልካቾች ከታች በቀረበው የኢሜይል አድራሻ እስከ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ  ፍላጎታችሁን መግለፅ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የኢሜይል አድራሻ፡- [email protected]

ስልክ ቁጥር፡- 00251-913564425