የግዮን ሆቴሎች ድርጅት አትክልትና ፍራፍሬ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ አቅርቦቱን ለአሸናፊው ድርጅት መስጠት ይፈልጋል፡፡

Ghion-Hotel-logo-1

Overview

 • Category : Food Items Supply
 • Posted Date : 07/23/2022
 • Phone Number : 0115513222
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/12/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዮን ሆቴሎች ድርጅት አትክልትና ፍራፍሬ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ አቅርቦቱን ለአሸናፊው ድርጅት መስጠት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም

 • የ2014/ 2015 የታደሰ የንግድ ፍቃድ ሰርተፍኬት ያለው
 • የታደሰ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
 • Tin No /የግብር መለያ ቁጥር/ ሰርተፍኬት ያለው
 • Vat/ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያለው
 • በአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ቢያንስ ከአስር አመት በላይ ልምድ ያለው
 • በተለያዩ ሆቴሎችና ትላልቅ ተቋማት ሦስት አመት እና ከዚያ በላይ በአትክልትና ፍራፍሬ አቅርቦት ልምድ ያለው እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችል
 • የአትክልት ማከማቻ መጋዝኑ ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ ከሚመለከተው ተቋም ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
 • የአትክልትና ፍራፍሬ ማጓጓዣ ምቹ የሆነ ተሸከርካሪ (መኪና) ያለውና ለሚታዘዘው አትክልትና ፍራፍሬ በራሱ ተሸከርካሪ ሆቴሉ ድረስ ማቅረብ የሚችል
 • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
 • ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታው ሰነድ ከድርጅታችን ግዥ አገልግሎት ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
 • የጨረታው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ21ው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
 • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115513222 Ext. 5429/5163 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
 • የሥራ ሰዓት፡ ከሰኞ እስከ ሀሙስ ጠዋት 2፡00 – 6፡00      ከሰዓት 7፡00 – 11፡00                አርብ ጠዋት ከ2፡00 – 5፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡00

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡