የጎተራ ኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ የህብረት ስራ ማህበር በመኪና መግቢያና መውጪያ ላይ ሙሉ ወጪውን በመቻል አውቶማቲክ ስማርት ካርድ ማከፋፈያ ማቆሚያ(Automatic Smart RFID card dispenser parking) ተከላውን የሚያከናውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Software purch. & Dev. Service
 • Posted Date : 10/24/2022
 • Phone Number : 0114702254
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/02/2022

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጎተራ ኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ የህብረት ስራ ማህበር በመኪና መግቢያና መውጪያ ላይ ሙሉ ወጪውን በመቻል አውቶማቲክ ስማርት ካርድ ማከፋፈያ ማቆሚያ(Automatic Smart RFID card dispenser parking) ተከላውን የሚያከናውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

 1. ማንኛውም በህጋዊ መንገድ የተቋቋመ ተጫራች በዘርፉ ልምድ ያለው፣ የታደሰ አውቶማቲክ ስማርት ካርድ ማከፋፈያ ማቆሚያ ተከላ ወይም ተዛማች ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ስም የምስክር ወረቀት፣የታደሰ የንግድ ምዝገባ፣የአሁኑ ዓመት ግብር ከፋይ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቲን መመዝገቢያ ሰርተፍኬት ያለው እና ማቅረብ የሚችል፡፡
 2. የማህበሩ ድርሻ/ግዴታ ለተከላ የሚሆነውን ቦታ ዝግጁ ማድረግ ብቻ እና ምንም አይነት ወጪ የማያወጣ ሲሆን ተጫራቹ የተከላውን፣የሰራተኞች ቅጥር፣የማኔጅመንት ስራውንና ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎች ራሱ የሚችል ሲሆን ከስራው የሚገኘውን ትርፍ በጋራ የሚካፈል ይሆናል፡፡
 3. ተጫራቾች የማሽኑን እና ተያያዥ የሆኑ ተጨማሪ ዕቃዎች(Accessory) እንዲሁም የተከላውን ዋጋ በተጨማሪም የሚገኘውን ትርፍ አከፋፈል በፐርሰንት በማስቀመጥ በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
 4. ተጫራቾች የፋይናንሽያል ሰነዱን ከአንድ ኮፒ ጋር በፖስታው ላይ ኮፒ እና ኦርጅናል በማለት ጽፈው ሁለት ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
 5. ተጫራቾች ይህ ግልጽ ጨረታ በወጣ ሰባት የስራ ቀናቶች ውስጥ ሰነዱን ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በስምንተኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
 6. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 7. ተጫራቾች ማህበሩ ጽ/ቤት በመሄድ በተጫራቾች የሚሞላ ለጨረታው የሚያስፈልጉ ነጥቦችን የያዘ ሰነድ መውሰድ ይኖርባችኋል፡፡

Þ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 0114 70 22 54/0114 70 12 47