የጨረታ ማስታወቂያ አዋሽ ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተገለፁትን ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለ በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 01/14/2023
- Phone Number : 0115570075
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/16/2023
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
አዋሽ ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተገለፁትን ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለ በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ተ.ቁ. | የተበዳሪው ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የንብረት አስያዥ ስም | የቦታ አገልግሎት | ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ | የካርታ ቁጥር | የቦታ ስፋት በካ.ሜ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የጨረታ ቀን | የጨረታ ሰዓት | ||
ከተማ | ክፍለ ከተማ | ቀበሌ /ወረዳ | ||||||||||
1 | ኢትዮ አሜሪካን አጠቃላይ ሆስፒታል | ኤርፖርት | ተበዳሪው | ለሆስፒታል አገልግሎት በተፈቀደ ይዞታ ላይ ያረፈ B+G+5 ህንጻ | አ.አ | ን/ስ/ላፍቶ | 08 | ድ/0244/2000/22344/01 | 3000 | 90,000,000 | 8-6-15 | 4፡00-5፡00 |
2 | ደገፋ ጃፊ | ነቀምቴ | ተበዳሪው | G+3 ለንግድ | ነቀምቴ | 717/W/L/EN/02 | 4140 | 12,000,000 | 8-6-15 | 4:00-5:00 | ||
3 | አምሳሉ ኦላና | ቡርቃ ጃቶ | ተበዳሪው | ለመኖርያ ቤት | ነቀምቴ | 3469/W/M/M/L/M/11 | 200 | 550,000 | 8-6-15 | 5፡00-6፡00 | ||
4 | አበበች ሻንቆ | ቡሌሆራ | ተበዳሪዋ | ለንግድ | ቡሌሆራ | BH/758/A.2545/2006 | 500 | 450,000 | 8-6-15 | 5:00-6:00 | ||
5 | ግርማ ጅሎ | ያቤሎ | አባቱ ግርማ | የመኖሪያ ቤት | ፊንጫዋ | – | – | BMF26/3138/06 | 400 | 425,000 | 8-6-15 | 9፡00-10፡00 |
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ባለዕዳው ወይም ሕጋዊ ወኪሉ፣ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት የባንኩ ዋናው መ/ቤት ጊዜያዊ ጽ/ቤት በሚገኝበት ህንጻ በሚገኘው የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር ቢሮ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ከተራ ቁጥር 2-5 የተዘረዘሩት ንብረቶች ጨረታ ደግሞ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ንብረቶቹ በሚገኙበት ግቢ ውስጥ ይካሄዳል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ግን ባንኩ ዋጋውን የሚቀበል መሆን አለመሆኑን ጨረታው ከተደረገበት ቀን ቀጥሎ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ለተጫራቹ ያሳውቃል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች የአሸናፊነት ደብዳቤ ከባንኩ ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ከመኖሪያ ቤቶች ውጭ ባሉ ንብረቶች ሽያጭ ላይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የሚታሰብ ሲሆን ሁሉንም ንብረቶች በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያ ገዢ ይከፍላል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ፡፡- ኤርፖርት ቅርንጫፍ 0116-18 06 11፣ ነቀምቴ ቅርንጫፍ 0576 -61 70 92፣ ቡርቃ ጃቶ ቅርንጫፍ 0576-608129፣ቡሌሆራ ቅርንጫፍ 0464-43 01 21 ፣ያቤሎ ቅርንጫፍ 0464-46 01 97 ወይም የሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 0115-57-00-75 ብሎ መደወል ወይም በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል፡፡
8 ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዋሽ ባንክ