የፋና ቦሌ ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር አማካሪ ለመቅጠር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

Overview

  • Category : Baseline Consultancy
  • Posted Date : 01/10/2023
  • Phone Number : 0911234747
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/20/2023

Description

ቀን፡-17/04/2015 ዓ.ም

አማካሪ ለመቅጠር  የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

   የፋና ቦሌ ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 የሚገኝና ከ500 ሰራተኞች በላይ በቋሚነት የያዘ በቦርድ የሚተዳደር የህዝብ ተቋም ነው ፡፡

ድርጅቱ አሁን ካለበት አቋም በመነሳት ወደ ፊት የአምስት (5) እና የአስር ዓመት (10) ዓመት እስትራቴጂክ ጥናት እንዲሰራለትና መዋቅር ተዘጋጅቶ ለፋይናንስ ፣ለሰው ሀይል ፣ ለደንበኞች አገልግሎት እንዲሁም ለሌሎች ክፍሎች የማንዋል ዝግጅትን ጨምሮ ሰርቶ እስከ ስድስት ወር ክትትል አድርጎ ተፈፃሚነቱን የሚያረጋግጥ ልምድና ውጤታማ ተቋም በጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ፡፡

ስለሆነም ለመጫረት ፈላጎቱ ያላችሁና የጨረታውን አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅታችንን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር መነሳሳቱ ያላችሁ ተቋማት ዝርዝር መረጃውን ከድርጅታችን መስሪያ ቤት ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ሥራ/ማህበር 17/18 ማዕከል የጨረታ ሰነድ በማይመለስ (100) አንድ መቶ ብር እየገዛችሁ በመውሰድ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል ፡፡

የማቅረቢያ ጊዜ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ትችላላችሁ ፡፡

  • ለበለጠ መረጃ ፡-በስ.ቁ 0911234747/0118229472 ማብራሪያ ታገኛላችሁ !!