የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በስሩ ከሚገኙ ለተለያዩ ለንግድ/ለድርጅት አገልግሎት የሚውሉ 105 የሚሆኑ ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/04/05/2015 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : House & Building Rent
 • Posted Date : 01/21/2023
 • Phone Number : 0118553617
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 02/08/2023

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/04/05/2015

 1. የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በስሩ ከሚገኙ ለተለያዩ ለንግድ/ለድርጅት አገልግሎት የሚውሉ 105 የሚሆኑ ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/04/05/2015 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
 2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የንግድ ቤቶች ኪራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ የኪራይ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው፡፡
 4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ከጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም አስከ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድን በኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመሰብሰቢ አደራሽ 1ኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ወይም ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም ቀን ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሀያ አምስት ሺ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌደራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
 6. ተጫራቾች የንግድ ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
 7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

      ለተጨማሪ መረጃ  

በስልክ ቁጥር 011-8-55-36-17 ወይም 011-5-58-48-90 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ዌብሳይት/ website www.fhc.gov.et

የፖ.ሣ.ቁ. P.O. Box 299

ፋክስ ቁጥር፡ 011-5-54-60-45/ 011-5-52-46-46