የፍ/ባለመብት አቶ ብስራት ይልማ ገ/ኪሮስ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሪት መሰለች ይልማ ኪሮስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/132783 በ9/10/2014 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ. 141204 በ23/10/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥር 9 ቀን 2015 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የ

Overview

  • Category : Industry & Factory Foreclosure
  • Posted Date : 12/24/2022
  • Phone Number : 0911218960
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/19/2023

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/መ/ቁ/ 132783

የፍ/አፈ/መ/ቁ. 39029

የፍ/ባለመብት አቶ ብስራት ይልማ ገ/ኪሮስ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሪት መሰለች ይልማ ኪሮስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/132783 በ9/10/2014 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ. 141204 በ23/10/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤት ቁጥር 1244/ሀ የሆነው የከብት እርባታ ድርጅት በካ/ቁ/24056 በሆነ ተመዝግቦ የሚገኝ ካርታ ያለው እና የካ/ቁ.24056 እና ቦሌ 13/28/4/11/24056/16702/01 ተመሳሳይ ይዞታ ላይ መሆኑ የቦታው ስፋት 2706 ካ/ሜ ስፋት ያለው 882 ካ/ሜ መንገድ የሚነካው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 2,541,240 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ አርባ አንድ ሺ ሁለት መቶ አርባ ብር)  የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥር 9 ቀን 2015 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛትየሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን  ግምት ¼ ኛውን በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

  • ከቦሌ ሆምስ በቦሌ ኤርፖርት VIP መውጫ አድርጎ ወደ የረር ጉሮ አዲሱ የሚሠራው መንገድን ይዞ የድሮው ጉምሩክ ወይም ኤቢሲ መኪና ኪራይ ፊት ለፊት ከፌዴራል ፖሊስ ቢሮ አጠገብ መንገድ ዳር ያለው መጋዘን ቤት እና ቦታ፤
  • የቦታ ስፋት 1824 ካ/ሜትር
  • ለአፓርትመንት፣ ለሆቴል፣ ለት/ቤት፣ ለሆስፒታል መገንቢያ የሚሆን፤

ለበለጠ መረጃ

በሞባይል ቁጥር፡- 0911 21 89 60 / 0966 80 95 53